የማሊ-ሩሲያ ትብብር፦ ባማኮ 65,500 ቶን ስንዴ በኮናክሪ ወደብ በኩል ተረከበች ከሞስኮ ለባማኮ የተበረከተ 65,500 ቶን የስንዴ ሰብዓዊ ጭነት በጊኒ ኮናክሪ ወደብ በኩል መድረሱን የብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ አርቲጂ ዘግቧል። ስንዴው በየብስ ተጓጉዞ በማሊ ዋና ከተማ የሚደርስ ይሆናል። ወደቡን የጎበኙት በጊኒ የማሊ አምባሳደር ማማዱ ኬይታ፤ ጭነቱን ከመርከቡ በፍጥነት ለማውረድ የሚረዱ አራት መጋዘኖች መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። አምባሳደሩ “ከሩሲያ ህዝብ ጋር ላለው የወንድማማችነት ግኑኝነት” አድናቆታቸውን ገልጸው፤ ጊኒ የስንዴ ጭነቱን በማስተናገድ ላደረገችው ድጋፍ አመስግነዋል። በ2023 እና 2024 መካከል ስድስት የአፍሪካ ሀገራት በአጠቃላይ 200,000 ቶን ነፃ የሩሲያ እህል አግኝተዋል። እርዳታው ቭላድሚር ፑቲን በ2023 ሰኔ ወር በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የስንዴ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ከገቡ በኋላ የመጣ ነው። ከዚህም ውስጥ ባማኮ 25,000 ቶን ስንዴ የተረከበች ሲሆን፤ ይህም ከሀገሪቱ የስንዴ ምርት ፍላጎት 6% የሚሆነውን ይሸፍናል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የማሊ-ሩሲያ ትብብር፦ ባማኮ 65,500 ቶን ስንዴ በኮናክሪ ወደብ በኩል ተረከበች
የማሊ-ሩሲያ ትብብር፦ ባማኮ 65,500 ቶን ስንዴ በኮናክሪ ወደብ በኩል ተረከበች
Sputnik አፍሪካ
የማሊ-ሩሲያ ትብብር፦ ባማኮ 65,500 ቶን ስንዴ በኮናክሪ ወደብ በኩል ተረከበች ከሞስኮ ለባማኮ የተበረከተ 65,500 ቶን የስንዴ ሰብዓዊ ጭነት በጊኒ ኮናክሪ ወደብ በኩል መድረሱን የብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ አርቲጂ ዘግቧል። ስንዴው በየብስ ተጓጉዞ... 31.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-31T18:14+0300
2024-12-31T18:14+0300
2024-12-31T18:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የማሊ-ሩሲያ ትብብር፦ ባማኮ 65,500 ቶን ስንዴ በኮናክሪ ወደብ በኩል ተረከበች
18:14 31.12.2024 (የተሻሻለ: 18:44 31.12.2024)
ሰብስክራይብ