የሩሲያው ሮስኮስሞስ ኩባንያ በጎርጎሮሳውያኑ 2033-2035 የኑክሌር ኃይል ማመንጫ መሳሪያን ወደ ጨረቃ ለማድረስ አቀደ

ሰብስክራይብ
የሩሲያው ሮስኮስሞስ ኩባንያ በጎርጎሮሳውያኑ 2033-2035 የኑክሌር ኃይል ማመንጫ መሳሪያን ወደ ጨረቃ ለማድረስ አቀደ“የዓለም አቀፉ ሳይንሳዊ የጨረቃ ጣቢያ ልማት ከቻይናና ከሌሎች ሀገራት ጋር በትብብር እየተከናወነ ነው። ሩሲያ ለፕሮጀክቱ ካላት አስተዋፅኦ አንፃር በጎርጎሮሳውያኑ 2033-2035 የኑክሌር ኃይል ማመንጫ  ወደ ጨረቃ ለማድረስ እና ለመትከል አቅዳለች" ሲል መግለጫው ገልጿል።ሩሲያ እና ቻይና በጎርጎሮሳውያኑ ህዳር 2022 በ የዓለም አቀፉ ሳይንሳዊ የጨረቃ ጣቢያ ልማትን  በጋራ ለመፍጠር ስምምነት ተፈራርመዋል። የሮስኮስሞስ ኃላፊ ዩሪ ቦሪሶቭ ባለፈው የፀደይ ወቅት፤ የሩሲያ እና የቻይና የጠፈር ድርጅቶች በጋራ ፕሮጀክታቸው አካል የሆነውን በጨረቃ ላይ የኑክሌር ኃይል ተቋም ለመትከል እያሰቡ ነው፣ እናም  ልማቱ ተጀምሯል ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0