እስራኤል ከጋዛ ሰርጥ የሚወጡ ወታደሮቿን ካርታ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም በማለት የሀማስ ባለስልጣን ተናገሩ ሀማስ ባለፈዉ ረብዑ ፤ በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ወታደሮችን ስለማስወጣት ፣ የተኩስ አቁም ስምምነትን በተመለከተ እና የእስረኛ ልውውጥ አስመልክቶ እስራኤል "አዲስ ሁኔታዎችን" አስቀምጣለች በማለት ተናግረዋል። " በአሁኑ ጊዜ ጠላታችን (እስራኤል) ወታደሮቿ ከጋዛ ሰርጥ የሚወጡበትን ግልፅ የሆነ ካርታ ለመሰጠት ፍቃደኛ አይደለችም ፤ በየት እና እንዴት እንደሚወጡ ማሳወቅ አትፈልግም። ጦርነቱን ለማቆም ግልፅ እና የመጨረሻ ቃላትን ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም" በማለት የሀማስ የፖሎቲካ ቢሮ አባላት የሆኑት ባስም ናም ለስፑትኒክ ተናግረዋል። ናም ጨምረውም ባለቤትነታቸው ፍልስጤም ቡድኖች የሆኑ የጦር መሳሪያዎች ጉዳይ በተኩስ አቁሙም ሆነ በጋዛ ሰርጥ እስረኛ ልውውጥ ድርድር ወቅት ያለመነሳቱን ጠቅሰዋል። " የኛ አቋም በሁለቱም ድርድሮች እና በሌሎችም ፣ የፍልስጤም ህዝቦች ናቸው እነርሱ በሀይል ተይዘዉ እስካሉ ድረስ ፤ ራሳቸውን ከሀይል አገዛዝ ነፃ የመውጣት እና የራሳቸውን ሀገር እስኪመሰርቱ ድረስ ፤ በሀይል መያዛቸውን በማንኛውም ህጋዊ ሁኔታ የመቃወም መብት አላቸው ይሄ ታጥቆ ማመፅንም ያካትታል" በማለት ተናግሯል። በእገታው ላይ የመጀመሪያው ድርድር ከተደረገ ከአንድ አመት በኋላ እስራኤል እና ሀማስ ድርድራቸውን በአሸማጋዩች አማካኝነት የቀጠሉ ሲሆን ስለቀሪ ታጋቾች እየተደራደሩ ይገኛሉ። በቅርቡ በካይሮ እና በዶሃ ውጥረቶች የበዛባቸው ንግግሮች እየተካሄዱ ሲሆን የታየ መሻሻል አለመኖሩን ምንጮች ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
እስራኤል ከጋዛ ሰርጥ የሚወጡ ወታደሮቿን ካርታ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም በማለት የሀማስ ባለስልጣን ተናገሩ
እስራኤል ከጋዛ ሰርጥ የሚወጡ ወታደሮቿን ካርታ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም በማለት የሀማስ ባለስልጣን ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
እስራኤል ከጋዛ ሰርጥ የሚወጡ ወታደሮቿን ካርታ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም በማለት የሀማስ ባለስልጣን ተናገሩ ሀማስ ባለፈዉ ረብዑ ፤ በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ወታደሮችን ስለማስወጣት ፣ የተኩስ አቁም ስምምነትን በተመለከተ እና የእስረኛ ልውውጥ አስመልክቶ... 29.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-29T17:01+0300
2024-12-29T17:01+0300
2024-12-29T17:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
እስራኤል ከጋዛ ሰርጥ የሚወጡ ወታደሮቿን ካርታ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም በማለት የሀማስ ባለስልጣን ተናገሩ
17:01 29.12.2024 (የተሻሻለ: 17:44 29.12.2024)
ሰብስክራይብ