የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ያነሱት ዋና ነጥቦች

ሰብስክራይብ
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ያነሱት ዋና ነጥቦች በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ስላለው ግንኙነት፤▫ ስትራቴጂካዊ የኑክሌር መሳሪያዎቿን በማዘመን ሩሲያ በስትራቴጂካዊ የጦር መሳሪያ ቅነሳ ስምምነት (ስታርት ስምምነት) ውስጥ የተቀመጡትን ገደቦች ሙሉ በሙሉ ማክበሯን ቀጥላለች።▫ ሩሲያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በሚኖሯት የሚሳኤል እና የኑክሌር ግንኙነት ውስጥ ተቀባይነት ያለው የትንበያ ደረጃን ለመጠበቅ በርካታ እርምጃዎችን ተግባራዊ  ማድረግ ለመቀጠል ዝግጁ ናት ።▫ ሩሲያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ሊገመት የሚችል የኑክሌር ሚሳይል ግንኙነትን ለማረጋገጥ የተለያዩ እርምጃዎችን ለመውሰድ ፈቃደኛ ናት።▫ ዋሽንግተን የፀረ-ሩሲያ አቋሟን እስካልቀየረች ድረስ ሩሲያ ከአሜሪካ ጋር የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ውይይት ላይ አትሳተፍም።▫ አሜሪካ እና ኔቶ ለሩሲያ አዲስ የሚሳይል ጉዳት ቢፈጥሩ ከሞስኮ በወታደራዊ-ቴክኒካል መልሶ ማጥቃት መልክ የኢምቢተኝነት አጸፋን ይቀበላሉ።▫ ሩሲያ የመካከለኛ እና የአጭር ርቀት የመሬት ሚሳኤሎችን በማሰማራት ላይ ያላትን የአንድ ወገን ጊዜያዊ እገዳ ትተዋለች፤ ይህም ዛሬ ተግባራዊ የማይሆን ቢሆንም ተጽዕኖው ግን ይኖራል።🪖የዩክሬንን ግጭት በተመለከተ፤▫ የዩክሬን ጦር ኃይሎችን ለማጠናከርና ዳግም ለማደራጀት የኬቭ አመለካከት እና ምዕራቡ ዓለም ውይይት ውጤታማ አይደለም፤ መፍትሄው ሊመጣ የሚችለው የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያቀረቡትን ሀሳብ ተግባራዊ በማድረግ ብቻ ነው።▫ ሞስኮ በዩክሬን ዙሪያ ያለውን ሁኔታ ለመፍታት ለድርድር ዝግጁ ናት፤ ነገር ግን የቀውሱ መነሻዎችን ለማጥፋት እና "በመሬት ላይ ያለውን" እውነተኛ ሁኔታን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።▫ የዴንማርክ ሁለተኛው ምድብ  F-16 ተዋጊ አውሮፕላኖችን ለኬቭ ማቅረባቸው የዩክሬንን ግጭት የበለጠ እንዲባባስ በማድረግ ሩሲያ ወታደራዊ-ቴክኒካዊ ባህሪ ያላቸውን ጨምሮ ተገቢ እርምጃዎችን እንድትወስድ አስገድዷታል። በሩሲያ እና ኢራን መሀከል የተፈረመውን የአጋርነት ስምምነት በተመለከተ ፤▫ ሩሲያ እና ኢራን አጋርነት ለተፈራረሙባቸው የፀጥታ ፣ የመከላከያ  እና የፀረሽብርተኝነት ትብብሮች ያላቸውን ቁርጠኝነት በአዲስ ሰምምነት የሚያሳዩ ይሆናል።▫ በሩሲያ እና በኢራን መሀከል ያለው የእስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ለፊርማ የተዘጋጀ እና በሶሪያ ያለው  ሁኔታ በስምምነቱ ላይ ምንም አይነት ለውጥ አላመጣም። ▫ በሩሲያ እና በሞስኮ መሀከል የሚፈረመው አዲስ ስምምነት በሞስኮ እና በቴህራን መሀከል ያለውን ትብብር በተለይም በፀጥታ እና በመከላከያ ዘርፍ የማሳደግ ፍላጎት ያሳያል። በሶሪያ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ▫ ሞስኮ በሶሪያ አዲስ ባለስልጣናት ፤ በሶሪያ ያላትን የጦር ሰፈር አስመልክቶ ያደረጉትን ማሻሻያ አለማወቋን እንዲሁም ይህንኑ አስመልክቶ ከደማስቆ የተላለፈላቸው ጥያቄ እንደሌለ ተናግረዋል።▫ በሶሪያ ያለውን  የሩሲያ የጦር ሰፈር አስመልክቶ የስራ ሁኔታ እና የጥገና ጉዳዩችን አስመልክቶ ከአዲሱ አስተዳደር ጋር ድርድር ሊኖር ይችላል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0