ሩሲያ እና ማሊ ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር  በኃይል ዘርፍ ፣ በግብርና እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ እያሰፉት መሆኑን የሩሲያው አምባሳደር ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ማሊ ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር  በኃይል ዘርፍ ፣ በግብርና እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ እያሰፉት መሆኑን የሩሲያው አምባሳደር ተናገሩ"የሩሲያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር አሌክሳንደር ኖቫክ በታህሳስ ወር መጀመሪያ በባማኮ በነበራቸው ጉብኝት ወቅት ፤  በጎንዩሽ ሩሲያ እና ማሊ ያላቸውን  ኢኮኖሚያዊ  ግንኙነቶች ለማጠናከር እና ለማሳደግ እንዲሁም በሀይል ዘርፍ ፣ በትራንስፖርት ፣ በመሰረተ ልማት ፣ ግብርና እና ማእድን ዘርፍ ያላቸው ትብብር ማሳደጊያ መንገዶችን ተነጋግረዋል። ይህ ሰምምነት የሀገራቱን የጋራ ጥቅም እና የወደፊት  የልማት እቅድ ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የተካሄደ ነው" በማለት በማሊ የሩሲያ አምባሳደር ኢጎር ግሮምይኮ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል። ሁለቱ ሀገራት አነስተኛ መጠን ያለው የኑክሌር ኃይል ማበልፀጊያ ስለ መገንባት እና የፀሀይ ብርሀን ጣቢያ ስለማቋቋም ውይይት አድርገዋል በማለት ግሮምይኮ አስረድተዋል።የሩሲያው የመንግስት የኑክሌር ድርጅት የሆነው ሮሳቶም የኑክሌር ማምረቻውን መሰረተ ልማት እና ስልጠናዎችን የሚመለከተው የስምምነት ላይ ተሳትፎ አድርጓል። ባለፈው ግንቦት 200 ሜጋዋት ማምረት የሚችል ከፀሀይ ብረሀን የሚገኝ ኃይል ማምረቻ በሮሳቶም ባለቤትነት በሚተዳደረው የኖቫቪንድ ድርጅት አማካኝነት ግንባታው እየተካሄደ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0