አዲስ አበባ በሚገኘው ዘዉዲቱ ሆስፒታል አንዲት እናት ስድስት ኪሎግራም የሚመዝን ህፃን መውለዷ ተሰማ

ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ በሚገኘው ዘዉዲቱ ሆስፒታል አንዲት እናት ስድስት ኪሎግራም የሚመዝን ህፃን መውለዷ ተሰማ የሆስፒታሉ  የፅንስ እና የማህፀን ክፍል ኃላፊ ዶክተር ረታ ትእዛዙ እንዳሉት አዲስ የተወለደው ህፃን በጤንነት ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከመፋፋቱ ጋር ተያይዞ ሊያጋጥሙት የሚችሉ የጤና ችግሮችን በቅርበት ለመከታተል በጨቅላ ህፃናት መቆያ ውስጥ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል። ዶክተሩ አክለውም በስራ ዘመናቸው ይህንን ያህል ክብደት ያለው ህፃን ሲወለድ የመጀመሪያቸው እንደሆነ ተናግረዋል።ዶክተሩ አክለውም ስድስት ኪሎግራም የሚመዝነውን ህፃን የወለደችው እናት በጤንነት ላይ የምትገኝ እንዲሁም የስኳር ክትትሏን እያካሄደች ነው።ምስል ከዘዉዲቱ ሆስፒታል መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0