በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በዓለም ዙሪያ በሰው ልጆች ምክንያት በተከሰተ የአየር ንብረት ለውጥ ቢያንስ 3,700 ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸውን ጥናት አመላከተ "በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በ26 የአየር ሁኔታ ላይ ባደረግነው ጥናት የአየር ንብረት ለውጥ ቢያንስ የ3,700 ሰዎች ሞት እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀል አስከትሏል... በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው የአየር ንብረት ለውጥ በ2024 በአማካይ 41 ተጨማሪ ቀናት አደገኛ ሙቀትን የጨመረ ሲሆን ይህም የሰዎችን ጤንነት ስጋት ላይ ጥሏል" ሲል ወርልድ ዌዘር አተሪቢዩሽን እና ክላይሜት ሴንትራል የጋራ ሪፖርት ገልጿል።ሪፖርቱ “በጣም ተጸኖ ባስከተለ” የአየር ሁኔታዎች ላይ የተገደበ በመሆኑ ከመጠን ባለፈ የአየር ሁኔታ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር "በአስር ወይም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ" ሊሆን እንደሚችል በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል።አደገኛ የሙቀት ቀናት የተከሰተባቸው አብዛኞቹ ሀገራት በትናንሽ የደሴት ሀገሮች እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ውስጥ መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል።በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በዓለም አቀፍ ደረጃ ክብረወሰን የሰበረ ከፍተኛ የሙቀት መጠን እንዲሁም ክብረወሰን የሰበረ ዝናብ እንዲዘንብ አድርጓል፤ ይህም የሆነው በሪፖርቱ ከተጠኑት 16 የጎርፍ አደጋዎች ውስጥ 15 የሚሆኑት በአየር ንብረት ለውጥ የተጠናከረ ዝናብ ምክንያት የተከሰቱ በመሆናቸው ነው። በተመሳሳይ ጊዜ የአማዞን ደን እና የፓንታናል እርጥብ አካባቢዎች በከባድ ድርቅና በዱር እሳት የተጠቁ ሲሆን ይህም ከፍተኛ የሆነ የብዝሃ ሕይወት መጥፋት አስከትሏል ሲል ሪፖርቱ ጠቁሟል።ወርልድ ዌዘር አተሪቢዩሽን እና ክላይሜት ሴንትራል ከቅሪተ አካል ከሚገኝ ኢነርጂ ፈጣን ሽግግር እንዲደረግ፣ ለታዳጊ አገራት ተጨማሪ ገንዘብ እንዲሰጥ፣ የሙቀት የሚከሰት ሞትን በወቅቱ ሪፖርት እንዲደረግ እና ለወደፊቱ የተጎጂዎችን ቁጥር ለመቀነስ የአየር ንብረት ክስተቶች ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንዲሻሻል ጥሪ አቅርበዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በዓለም ዙሪያ በሰው ልጆች ምክንያት በተከሰተ የአየር ንብረት ለውጥ ቢያንስ 3,700 ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸውን ጥናት አመላከተ
በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በዓለም ዙሪያ በሰው ልጆች ምክንያት በተከሰተ የአየር ንብረት ለውጥ ቢያንስ 3,700 ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸውን ጥናት አመላከተ
Sputnik አፍሪካ
በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በዓለም ዙሪያ በሰው ልጆች ምክንያት በተከሰተ የአየር ንብረት ለውጥ ቢያንስ 3,700 ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸውን ጥናት አመላከተ "በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በ26 የአየር ሁኔታ ላይ ባደረግነው ጥናት የአየር ንብረት ለውጥ ቢያንስ... 28.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-28T16:12+0300
2024-12-28T16:12+0300
2024-12-28T16:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በዓለም ዙሪያ በሰው ልጆች ምክንያት በተከሰተ የአየር ንብረት ለውጥ ቢያንስ 3,700 ሰዎችን ለሞት መዳረጋቸውን ጥናት አመላከተ
16:12 28.12.2024 (የተሻሻለ: 16:44 28.12.2024)
ሰብስክራይብ