የታህሳስ 19 ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦ የሴኔጋሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኡስማኔ ሶንኮ በጎርጎሮሳዊያኑ 2027 ሀገራቸው ወጪዎቿን በመቀነስ እና የምትሰበስበዉን ግብር በማሳደግ የበጀት ጉድለቱን በ3 በመቶ ለመቀነስ ማሰባቸው ተነገረ። የተመድ የፀጥታው ምክርቤት በትላንትናው እለት ለአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እና መረጋጋት የሱማሊያ ተልእኮ ኤዩሶም ተብሎ ትልቁን የአፍሪካ ህብረት የሽብር መከላከያ ተልእኮ በመተካት ከ ጎርጎሮሳዊያኑ ጥር 1,2025 ጀምሮ ስራ ለሚጀምረው አካል እውቅና ሰጠ። ናይጀሪያ ከምርጫ በኋላ በሞዛምቢክ የተፈጠረው ረብሻ እንዳሳሰባት አሳወቀች ፤ በተለይም ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ 250 ሞት የተመዘገቡባቸው በዋና ከተማዋ ማፑቶ እና ቤሪያን እንዳሁም ናምፑላ የመሳሰሉት ትልልቅ ከተሞች ሁኔታው እየተባባሰ ነው ብላለች። የሩሲያ ፌድራል የፀጥታ አገልግሎት በዩክሬን ልዩ አገልገሎት ፤ በሩሲያ ከፍተኛ የጦር ሀላፊ ላይ እና እየተካሄደ ያለውን ልዩ የጦር ኦፕሬሽን የሚፅፍ ጦማሪ ላይ የታቀደን የሽብር አደጋ መከላከሉን አስታወቀ። የሩሲያ የውጭ ደህንነት አገልግሎት የአሜሪካ እና የብሪታንያ ልዩ አገልግሎቶች በሶሪያ በሚገኘው የሩሲያ የጦር ሰፈር ላይ የሽብር ጥቃት ለማድረስ እየተዘጋጁ ነው በማለት ተናገረ። የሩሲያ አየር መከላከያ ኃይሎች 56 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ባለፈው ምሽት ማውደማቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የስሎቫኪያዎ ጠቅላይ ሚኒስትር ፊኮ እንዳሳወቁት የዩክሬን አመራሮች ሀገራቸውን ወደ ከፋ ችግር እያስገቧት ነው ፤ ለዚህ "የጀብዱ" አድራጎታቸው ግዛታቸውን በማጣት እና የውጭ ወታደሮችን በሀገራቸው በማቆየት የሚከፍሉ ይሆናል። የአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድቤት የቲክቶክን እገዳ እንዲያቆየው እና እርሳቸው ስልጣናቸውን ሲይዙ ችግሮቹን እንዲፈቱ ጠይቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የታህሳስ 19 ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦
የታህሳስ 19 ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦
Sputnik አፍሪካ
የታህሳስ 19 ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦ የሴኔጋሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኡስማኔ ሶንኮ በጎርጎሮሳዊያኑ 2027 ሀገራቸው ወጪዎቿን በመቀነስ እና የምትሰበስበዉን ግብር በማሳደግ የበጀት ጉድለቱን በ3 በመቶ ለመቀነስ ማሰባቸው ተነገረ። የተመድ የፀጥታው ምክርቤት... 28.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-28T12:58+0300
2024-12-28T12:58+0300
2024-12-28T13:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий