የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር የውጭ ወታደራዊ ቤዞችን ለመዝጋት መወሰናቸውን አስታወቁ

ሰብስክራይብ
የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር የውጭ ወታደራዊ ቤዞችን ለመዝጋት መወሰናቸውን አስታወቁኦስማኔ ሶንኮ ይህንን ያሳወቁት ለፓርላማው እስከ ጎርጎሮሳዊያኑ 2050 የተቀመጠውን የመንግስትን ስትራቴጂ በተመለከተ ባደረጉት የፖሊሲ ንግግር ላይ መሆኑ ሴኔጎ ፖርታል ዘግቧል። "መንግስት በሴኔጋል ግዛት የሚገኙ የውጭ ሀገራት ወታደራዊ ጣቢያዎችን በሙሉ ለመዝጋት ወስኗል" ብለዋል ሶንኮ። "ይህ ውሳኔ የብሔራዊ ሉዓላዊነትን ለማጠናከር እና የአገሪቱን የመከላከያ ፖሊሲ አቅጣጫን እንደገና ለመቀየር ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል" ሲሉም ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ እርምጃ በሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ተነሳሽነት የተወሰደ መሆኑን አስረድተዋል።በሀገሪቱ ዋና ከተማ ዳካር ውስጥ ወደ 300 የሚጠጉ ወታደሮች ያሏቸው ሦስት የፈረንሳይ ወታደራዊ ተቋማት ይገኛሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0