የታህሳስ 18 ዓበይት የዓለም ዜናዎች ፦

ሰብስክራይብ
የታህሳስ 18 ዓበይት የዓለም ዜናዎች ፦ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በሞዛምቢክ ከተካሄደው ተቃውሞ በኋላ የቆሰሉ እና የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውን ሚዲያዎች መዘገባቸውን ተከትሎ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጥሪ አቀረቡ ። የአፍሪካ ሁለተኛዋ ማር አምራች የሆነችው ታንዛንያ ፤ ለቻይና ገበያ የመጀመሪያ ዙር የማር ምርቷን መላኳን የሀገሪቱ የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ ። የሴኔጋሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኡስማኔ ሶንኮ በመጪው አመታት በሰፊው ሀገሪቷን በሚለውጥ መልኩ ለመትገበር ስላሰቡት ፖሊሲ  ለብሄራዊ ምክርቤት ንግግር ያደርጋሉ የደቡብ አፍሪካዉ የኃይል ድርጅት  የሆነው ሳሶል በሞዛምቢክ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ከሀገሪቱ ለደቡብ አፍሪካ የሚወስደውን የጋዝ መስመር ማቋረጡን እና በማምረቻው አካባቢ ባለው አለመረጋጋ ምክንያት ምርቱን  ማቆሙን የድርጅቱ ቃል አቀባይ አስታወቁ ። የሩሲያ የፀጥታ አገልግሎት የሩሲያን ነዋሪዎች ዘር ለሚለየው የፔንታጎን ስረአት መረጃ ሲሰበስብ የነበረውን አሜሪካዊ በቁጥጥር ስር አዋለ። የሩሲያ አየር መከላከያ በሩሲያ አምስት ክልል ውስጥ ፤ 13 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ባለፈው ምሽት መደምሰሱን የመከላከያ ሚኒስትር አስታወቀ። እስራኤል በየመን ባደረሰችው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ ስድስት አደገ ፤ 40 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል እንደ የሀውቲ መንግስት ጤና ሚኒስትር ዘገባ። በፍልስጤም የጋዛ ሰርጥ እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት 50 ሰዎች ሞቱ ፤ ከሟቾቹ አምስቱ የህክምና ባለሙያዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትር አስታወቀ። አሜሪካን የእዳ ሁኔታዋ የማይቀየር ከሆነ ወደ ኪሳራ (ባንክረፕሲ) ትሄዳለች በማለት ኤሌን መስክ ተናገረ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0