የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በአፍሪካ አዳዲስ የቢዝነስ ፕሮጀክቶች ትልቋ ኢንቨስተር መሆኗን የሚዲያ ግምት አሳየ

ሰብስክራይብ
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በአፍሪካ አዳዲስ የቢዝነስ ፕሮጀክቶች ትልቋ ኢንቨስተር መሆኗን የሚዲያ ግምት አሳየ ከ2019 እስከ 2023 የኤምሬትስ ኩባንያዎች ለታዳሽ ኃይል የገቡትን የ72 ቢሊዮን ቃል ጨምሮ፤ ለአፍሪካ ፕሮጀክቶች 110 ቢሊዮን ዶላር ፈሰስ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ይህ በአነስተኛ ትርፍ ምክንያት የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እየቀነሱ ከሚገኙት የእንግሊዝ፣ ፈረንሳይ ወይም ቻይና ኩባንያዎች ከእጥፍ በላይ ይበልጣል። የአፍሪካ መሪዎች በኮፕ29 የአየር ንብረት ፋይናንስ ቃል ኪዳኖች ደስተኛ አይደሉም። በጉባኤው የጸደቀው የ300 ቢሊዮን ዶላር የተስፋ ቃል ከተጠየቀው 1.3 ትሪሊዮን ዶላር አንጻር አነስተኛ ነው። "የአፍሪካ ሀገራት ለኃይል ሽግግራቸው ገንዘቡን ይፈልጉታል። የዩኤኢ ኢንቨስተሮች ምዕራባውያን መድፈን ያልቻሉትን ትልቅ ክፍተት ይሞላሉ” ሲል በቻተም ሀውስ ቲንክ ታንክ ተባባሪ ባልደረባ የሆነው አህመድ አቡዱህ ተናግሯል። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በአፍሪካ ወደቦች፣ አየር መንገዶች፣ ግብርና፣ ቴሌኮም፣ የካርቦን ክሬዲት እና ማዕድን ላይ ኢንቨስት የሚያደርጉ ሲሆን፤ በቅርቡም በዛምቢያ የመዳብ ማዕድን ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ አፍሰዋል። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መንግሥት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በአፍሪካ የሀገሪቱ ወቅታዊ አጠቃላይ ኢንቨስትመንት 60 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም በአህጉሪቱ አራተኛዋ ግዙፍ ኢንቨስተር ያደርጋታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0