የታህሳስ 16 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የታህሳስ 16 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 በአክታዉ የደረሰዉን የአውሮፕላን አደጋ ተከትሎ የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሀም አሊዬቭ ታህሳስ 17 የሀዘን ቀን እንዲሆን አወጁ። ከአደጋው በኋላ የአዘርባጃን አየር መንገድ ወደ ግሮዝኒ እና ማካቻካላ የሚደረገውን ሁሉኑም በረራ ሰርዟል። 🟠 የቀድሞው የቻይና ባለስልጣን ሊ ጂንዙ ከ60 ሚሊየን ዶላር በላይ በማጭበርበር የሞት ፍርድ ተላለፈባቸው። 🟠 የዩክሬን ጦር በሩሲያ ኩርስክ ክልል ሎጎቭ ከተማ በሲቪል ኢላማዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት አራት ሰዎች ሲሞቱ፤ አምስት በሚሆኑት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሰ። አንድ ባለ አምስት ፎቅ እና ሁለት ባለ አንድ ፎቅ የመኖሪያ ሕንፃዎች መውደማቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። 🟠 በሜዲትራኒያን ባህር በሰጥመችው የሩሲያ መርከብ ኡርሳ ሜጀር ላይ የሽብር ጥቃት መፈጸሙን የጭነት መርከብ ባለቤቱ ኦቦሮንሎጂስቲክስ ገለጸ። በመርከቡ ቀኝ ጎን በኩል የተከሰቱት ሶስት ፍንዳታዎች መርከቡ እንዲሰጠም መንስዔ እንደሆኑ ኩባንያው አስታውቋል። 🟠 የኪዬቭ መንግሥት በራሱ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መታጠቅ አይችልም፤ ይህ ሊሆን የሚችለው ከሌሎች ሀገራት ወሳኝ ግብዓቶችን ሲያገኝ ብቻ ነው ሲሉ፤ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0