በሞዛምቢክ የምርጫ ውጤት ተቃውሞ ባለፉት 24 ሰዓታት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ

ሰብስክራይብ
በሞዛምቢክ የምርጫ ውጤት ተቃውሞ ባለፉት 24 ሰዓታት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ መስከረም 29 በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ገዥው ፍሪሊሞ ፓርቲ ማሸነፉ ከተረጋገጠ በኋላ በሞዛምቢክ በተቀሰቀሰው ብጥብጥ፤ ሁለት የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ ቢያንስ 21 ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፓስኮል ሮንዳ ተናግረዋል። የሕገ-መንግሥታዊ ምክር ቤቱ የፍሬሊሞ እጩው ፊሊፔ ንዩሲ መጀመሪያ ይፋ ከተደረገው የውጤት ነጥብ ቢቀንስም ምርጫውን እንዳሸነፉ ማረጋገጡን ተከትሎ፤ በመላ ሀገሪቱ ተቃውሞ ተነስቷል። ሮንዳ በፖሊስ ጣቢያዎች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶችን ጨምሮ 236 ከባድ የኃይል ድርጊቶችን ሪፖርት አድርገዋል። ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "የታጠቁ ቡድኖች በስለታማ መሳሪያዎች እና ጠመንጃ በፖሊስ ጣቢያዎች፣ በማረሚያ ቤቶች እና በሌሎች መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል" ያሉ ሲሆን፤ ከ70 በላይ ሰዎች መታሰራቸውንም ጠቁመዋል። በማፑቶ በተቃዋሚዎች እና በፖሊስ መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ሰልፈኞች ቁሳቁሶችን ሲወረውሩ እንደነበርና የእሳት ቃጠሎ እንዳስነሱም ተሰምቷል። የተቀጣጠሉ የመንገድ መሰናክሎች የከተማዋን አንዳንድ ክፍሎች በጭስ ሸፍነዋልም ነው የተባለው። ብጥብጡ ካቦ ዴልጋዶ፣ ናምፑላ፣ ዛምቤዚያ እና ቴቴን ጨምሮ በተለያዩ ሰሜናዊ የሀገሪቱ ግዛቶች ተዛምቶ ሱቆች፣ ባንኮች እና ሌሎች የንግድ ተቋማት መዘረፋቸውንና መቃጠላቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0