በሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ የተመራ ልዑክ ለሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገባ

ሰብስክራይብ
በሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ የተመራ ልዑክ ለሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገባ የሶማሊያ የልዑካን ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከተመራ ልዑክ ጋር ውይይት አድርጓል። ውይይቱ፤ የአንካራውን ስምምነት ለማፅናት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ላይ ያነጣጠረ ነው። በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ የአንካራውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ቁርጠኛ መሆኗን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናግዋል። የሶማሊያ የውጭና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር በበኩላቸው ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በሶማሊላንድ ጉዳይ የገቡበትን አለመግባባት፤ ታኅሣሥ 2፣ 2017 ዓ.ም በተርክዬ አሸማጋይነት ለመፍታት መስማማታቸው ይታወቃል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0