ናይጄሪያ በዛምፋራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን ተከትሎ ለአምስት ዓመታት የቆየውን የማዕድን ፍለጋ ገደብ አነሳች በፈረንጆቹ 2019 በወርቅ፣ ሊቲየም እና መዳብ በበለፀገው የሀገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ ግዛት በሽፍቶች ጥቃት ምክንያት የተላለፈው ገደብ፤ ሕገ-ወጥ የማዕድን ፍለጋ እንዲስፋፋ አድርጓል ሲሉ የሀገሪቱ ጠጣር ማዕድን ሚኒስትር ዴሌ አላኬ ተናግረዋል። "የፀጥታ አካላት የወሰዱት ትልቅ እርምጃ የጸጥታ እጦት ደረጃው በጉልህ እንዲቀንስ አድርጓል፤ የፍለጋ ገደቡ በመነሳቱም የዛምፋራ የማዕድን ዘርፍ ቀስ በቀስ ለሀገሪቱ የገቢ አሰባሰብ አስተዋጽኦ ማድረግ ይጀምራል" ብለዋል። ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከ1% በታች የሚያበረክተውን የማዕድን ዘርፍ ለማሳደግ፤ ናይጄሪያ ስራ ያልጀመሩ ፈቃዶችን መሻር፣ ባለሃብቶች በአዲሱ ብሔራዊ ኩባንያ ውስጥ እንዲሳተፉ መፍቀድ እና የማዕድን ኤክስፖርትን መገደብ ጨምሮ ማሻሻያዎችን በመተግበር ላይ ትገኛለች። የሴክተሩን አቅም ለማሳደግ ናይጄሪያ ዓለም አቀፍ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍም ትሻለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ናይጄሪያ በዛምፋራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን ተከትሎ ለአምስት ዓመታት የቆየውን የማዕድን ፍለጋ ገደብ አነሳች
ናይጄሪያ በዛምፋራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን ተከትሎ ለአምስት ዓመታት የቆየውን የማዕድን ፍለጋ ገደብ አነሳች
Sputnik አፍሪካ
ናይጄሪያ በዛምፋራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን ተከትሎ ለአምስት ዓመታት የቆየውን የማዕድን ፍለጋ ገደብ አነሳች በፈረንጆቹ 2019 በወርቅ፣ ሊቲየም እና መዳብ በበለፀገው የሀገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ ግዛት በሽፍቶች ጥቃት ምክንያት የተላለፈው... 24.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-24T15:29+0300
2024-12-24T15:29+0300
2024-12-24T15:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ናይጄሪያ በዛምፋራ ክልል ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን ተከትሎ ለአምስት ዓመታት የቆየውን የማዕድን ፍለጋ ገደብ አነሳች
15:29 24.12.2024 (የተሻሻለ: 15:44 24.12.2024)
ሰብስክራይብ