የታህሳስ 15 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የታህሳስ 15 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የአፍሪካ ሀገራት ከአሜሪካ ጋር በባዮሎጂ-ወታደራዊ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር አስመልክቶ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ ሰጠ። 🟠 የደቡብ ኮሪያ ተቃዋሚዎች የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ-ዩልን እና ቀዳማዊት እመቤት ኪም ኪዮን ሂን ለመመርመር የሚያስችለውን ሕግ ባለመፈረማቸው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱን ሃን ዳክ-ሱን ሊከሱ እንደሚችሉ በድጋሚ ማስጠንቀቃቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። 🟠 በምዕራብ ቱርክ ባሊኬሲር ከተማ በፈንጂ ፋብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ 12 ሰዎች መሞታቸውን የውጭ መገናኛ ብዙሃን ገለጹ። 🟠 የሩሲያ የጭነት መርከብ ኡርሳ ሜጀር በሞተር ክፍል ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ሰጠመ። 14 የመርከቡ ሰራተኞች ሲድኑ ሁለቱ የገቡበት እንደማይታወቅ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። 🟠 በሩሲያ ሮስቶቭ እና ቮሮኔዝ ክልል አራት የዩክሬን ድሮኖች በአንድ ሌሊት ውስጥ መውደማቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0