የመጀመሪያው የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀመረ

ሰብስክራይብ
የመጀመሪያው የኢትዮ-ቻይና የፊልምና ቴሌቪዥን ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀመረ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የፊልም ፌስቲቫል የብሪክስ አባል ሀገራትን የፊልም ኢንዱስትሪ ትብብር የማጠናከር ግብ አንግቧል። ፌስቲቫሉ በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል የቱሪዝም፣ የባህል እና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር እንደሚረዳም ተገልጿል። በፌስቲቫሉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ፊልም ‘ሂሩት አባቷ ማነው’ን ጨምሮ ሌሎች የሁለቱ ሀገራት ፊልሞች ለዕይታ ይበቃሉ። በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያና ቻይና በኪነ-ጥበብ ቀደምት ስልጣኔ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል። ፌስቲቫሉም የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር የባህል ትውውቅን ለማሳደግ እንደሚረዳ ተናግረዋል። ፌስቲቫሉ እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0