የታህሳስ 14 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የታህሳስ 14 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የስሎቫክያ ጠቅላይ ሚንስትር ሮበርት ፊኮ ዩክሬን ከፈረንጆቹ ጥር 1 ቀን 2025 ጀምሮ የሩሲያን ጋዝ ለማጓጓዝ ፈቃደኛ እንደማትሆን እየገለጸች ባለበት ሰዓት እሁድ እለት ሞስኮ ገብተዋል። ፊኮ ይህ ውሳኔ ስሎቫኪያን ቀውስ  ውስጥ ይከታል ሲሉ ቀደም ሲል ተናግረዋል። 🟠 የአውሮፓ ሕብረት በአሁኑ ጊዜ በትራንስኒስትሪያ ግጭት ውስጥ ለመግባት ዝግጁ አይደለም ሲል የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት አስታውቋል። 🟠 በደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ሶስት ወታደር ያልሆኑ ሰዎች ቆስለዋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባልተለመዱ ሹመቶች ማስገረማቸውን ቀጥለዋል። የቀድሞ የአሜሪካ እግር ኳስ ተጫዋች የፕሬዝዳንቱን የክሪፕቶከረንሲ ምክር ቤት በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ተመርጠዋል። 🟠 የተባበሩት አውሮፕላን ኮርፖሬሽን (የሩሲያ ሮስቴክ ስቴት ኮርፖሬሽን አካል) ተጨማሪ ሱ-57 ተዋጊ ጀቶችን እና ሱ-34 ቦምቦ ጣይ ጀቶችን ለሩሲያ ወታደሮች አስረክቧል። 🟠 የዩክሬን ጦር በረዥም ርቀት ሚሳኤል ዶንዬትስክን እንዳጠቃ ሆኖም የአየር መቃወሚያዎች ውጤታማ እንደነበሩ የሩሲያ የጸጥታ አገልግሎት አስታውቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0