የአሜሪካ የባህር ኃይል በስህተት የራሱን ተዋጊ ጄት በቀይ ባህር ላይ መትቶ ጣለበዛሬው እለት የአሜሪካ ባህር ኃይል F/A-18 ተዋጊ ጄት የሁቲ ዒላማዎችን ለማጥቃት በመጓዝ ላይ እያለ በዩኤስኤስ ጌቲስበርግ ተመቶ ወድቋል።ሁለቱም አብራሪዎች በተሳካ ሁኔታ ተወርውረው በሕይወት ተርፈዋል፤ ነገር ግን አንደኛው ቀላል ጉዳት ደርሶበታል ሲል የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ገልጿል።የቱሩማን ኬሪየር ስትራይክ ግሩፕ አካል የሆነው ዩኤስኤስ ጌቲስበርግ ከሳምንት በፊት ወደ ቀጠናው የገባ ሲሆን አውሮፕላኑ ላይ ተኩስ ከፍቷል። F/A-18 አውሮፕላን የተነሳው ዩኤስኤስ ሂሪ ኤስ ትሩማን ከተሰኘው አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ነው።አሜሪካ ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር በመሆን የሁቲ አማፂያን ለፈጸሙት ጥቃት የአጸፋ ምላሽ በየመን ሰነአ በቡድኑ ኢላማዎች ላይ ከቅዳሜ ጀምሮ የአየር ድብደባ አድርሰዋል።ሁቲዎች ለፍልስጤማውያን ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በሚታመኑ መርከቦች ላይ ጥቃት የመሰንዘር ፖሊሲ አውጀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የአሜሪካ የባህር ኃይል በስህተት የራሱን ተዋጊ ጄት በቀይ ባህር ላይ መትቶ ጣለ
የአሜሪካ የባህር ኃይል በስህተት የራሱን ተዋጊ ጄት በቀይ ባህር ላይ መትቶ ጣለ
Sputnik አፍሪካ
የአሜሪካ የባህር ኃይል በስህተት የራሱን ተዋጊ ጄት በቀይ ባህር ላይ መትቶ ጣለበዛሬው እለት የአሜሪካ ባህር ኃይል F/A-18 ተዋጊ ጄት የሁቲ ዒላማዎችን ለማጥቃት በመጓዝ ላይ እያለ በዩኤስኤስ ጌቲስበርግ ተመቶ ወድቋል።ሁለቱም አብራሪዎች በተሳካ ሁኔታ... 22.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-22T19:46+0300
2024-12-22T19:46+0300
2024-12-22T20:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий