የዳርፉሩ ገዢ የአርኤስፍ አማፂዎች በኤል ፋሽር አቅራቢያ በሲቪል ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ግድያ አወገዙ " በደርዘን የሚቆጠሩ በደቡብ ኤል ፋሼር አቡ ዛሪጋ መንደር ሲኖሩ የነበሩ ያልታጠቁ ሲቪል ሰዎች ዘር እና ብሔራቸውን መሰረት በማድረግ በፈጥኖ ደራሹ አማፂ ሀይል ታጣቂዎች (አርኤስፍ) ተገድለዋል ፤ የአለምአቀፍ ድንጋጌዎች በመጣስ በዘምዘም ካምፕ እና ኤል ፋሼር ላይ በቦምብ የመደብደብ እና የማቃጠል ድርጊት ተፈፅሟል" በማለት የሱዳንዋ ዳርፉር ግዛት አስተዳዳሪ ሚኒ አርኮ ናዊ በማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ በዛሬው እለት ባወጡት መግለጫ ተጠቅሷል። በዛሬው እለት በትንሹ 38 ሰዎች በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ አል ፋሽር የፈጥኖ ደራሹ አማፂ ኃይሎች በተኮሱት ሚሳኤል መገደላቸውን የሲቪል አክቲቪስቶችን በመጥቀስ የአካባቢው ሚዲያ ዘግቧል። ይህ ጥቃት በአርኤስፍ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የደረሰበት እና ዘጠኝ ሰዎች የሞቱበት ፤ በሳውዲ አረቢያ የሚተዳደረው ብቸኛዉ የከተማው ሆስፒታል አርብ እለት መመታቱን ተከትሎ የተካሄደ ነው። ሁኔታው በእጅጉ የተባባሰው ከግማሽ ሚሊዩን በላይ ሰዎች ለከፍተኛ ረሀብ ሁኔታዎች ተጋልጠው የሚገኙበት በአካባቢው ያለው የዘምዘም የስደተኞች ካምፕ በአርኤስኤፍ ጥቃት ከደረሰበት በኋላ ነው። በዚሁ አማፂ ኃይል ጥቃት የተነሳ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተመድ ስር ያሉትን ካምፖች ጥለው ወጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የዳርፉሩ ገዢ የአርኤስፍ አማፂዎች በኤል ፋሽር አቅራቢያ በሲቪል ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ግድያ አወገዙ
የዳርፉሩ ገዢ የአርኤስፍ አማፂዎች በኤል ፋሽር አቅራቢያ በሲቪል ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ግድያ አወገዙ
Sputnik አፍሪካ
የዳርፉሩ ገዢ የአርኤስፍ አማፂዎች በኤል ፋሽር አቅራቢያ በሲቪል ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ግድያ አወገዙ " በደርዘን የሚቆጠሩ በደቡብ ኤል ፋሼር አቡ ዛሪጋ መንደር ሲኖሩ የነበሩ ያልታጠቁ ሲቪል ሰዎች ዘር እና ብሔራቸውን መሰረት በማድረግ በፈጥኖ ደራሹ... 22.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-22T13:58+0300
2024-12-22T13:58+0300
2024-12-22T14:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የዳርፉሩ ገዢ የአርኤስፍ አማፂዎች በኤል ፋሽር አቅራቢያ በሲቪል ዜጎች ላይ የፈፀሙትን ግድያ አወገዙ
13:58 22.12.2024 (የተሻሻለ: 14:14 22.12.2024)
ሰብስክራይብ