የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዳ ካቢኒአቸውን እንደገና እያዋቀሩ  መሆኑን ሪፖርቶች አመላከቱ

ሰብስክራይብ
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዳ ካቢኒአቸውን እንደገና እያዋቀሩ  መሆኑን ሪፖርቶች አመላከቱ   ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት አዳዲስ  የካቢኔቸውን አባላት ለቃለ መሃላ በሪዱአ መሰብሰቢያ አዳራሽ መጥራታቸውን ግሎባል የዜና ማሰራጫ ሁለት ምንጮቹን በመጥቀስ ዘግቧል። ይህ የካቢኔ እንደገና መዋቀር እየተደረገ  ያለው የፋይናንስ ሚኒስትሯ  ክርስትያ ፍሪላንድ ከስራ በለቀቁ ማግስት ነው። ፍሪላንድ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በዋና ዋና ወጪዎች ውሳኔ ላይ የነበራቸውን አለመስማማት በመጥቀስ ከካቢኔነታቸው ለቀዋል። በመልቀቂያ ደብዳቤዋ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሰተዳደር ፖሊሲ የሆነው "አሳሳቢ የኢኮኖሚ ብሄርተኝነት " እንዲሁም የ25 በመቶ ታሪፍ ጭማሪ ማስፈራሪያ "ከባድ ችግር" እንደሚፈጥር አብራርተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0