የሩሲያ ኢኮኖሚ እድገት ሚስጥሩ ባለፉት ሁለት አመታት የተከተለችው ትክክለኛ መንገድ  ነው በማለት ካሜሮናዊው የፋይናንስ ባለሙያ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ ኢኮኖሚ እድገት ሚስጥሩ ባለፉት ሁለት አመታት የተከተለችው ትክክለኛ መንገድ  ነው በማለት ካሜሮናዊው የፋይናንስ ባለሙያ ተናገሩ ሩሲያ " ትክክለኛ ያልሆነ ፣ ህገወጥ እና እንዲሁም ሰብአዊነት የሚጎድለው" የምእራባውያን ማእቀብ የተጣለባት ቢሆንም ፤  ሀገሪቷን ለመግንባት አጋር የምታደርጋቸውን ሀገራት ቁጥር በማሳደግ እና በማጠናከር ከቻይና ፣ ህንድ ፣ ኢራን ፣ እና ሰሜን ኮሪያ ጠንካራ አጋርነት መፍጠር ችላለች ሲሉ በትላንትናው እለት በሩሲያው መሪ የተነገረው የኢኮኖሚ እድገት ማሳያ ላይ ሀሳባቸውን ለስፑትኒክ የሰጡት ዢን ሬኔ ንዶኡማ ናቸው።ሩሲያ ብዙ የተፈጥሮ ሀብቶች አሏት፤ ነገርግን ይሄ  አልረዳትም ፤ " ከብዙ ሀገሮች ጋር የፈጠረችው አጋርነት በተለይም ከአፍሪካ ጋር ያላት ልዩ አጋርነት  እና ያደረጓቸው የገንዘብ እና የፋይናንስ ለውጦች ኢኮኖሚዋ እንዲሻሻል አድርገዋል" በማለት ንዶኡማ አፅንኦት ሰጥተውበታል።በባለፉት ሁለት አመታት የሩሲያ ኢኮኖሚ 8 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን እንዲሁም የሀገሪቷ ኢኮኖሚ ባለው እንቅስቃሴ ከአውሮፓ አንደኛ ከአለም አራተኛ መሆኑን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በትላንትናው እለት በነበራቸው የቀጥታ መስመር እና የጋዜጣው መግለጫ ላይ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0