አሜሪካ ኬንያዊ የጓንታናሞ እስረኛን ወደ ሀገሩ እንደመለሰች ፔንታጎን አስታወቀ ኬንያዊው ሞሐመድ አብዱል ማሊክ ባጃቡ፤ በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ ተቋም ውስጥ ከቀሩት 30 እስረኞች አንዱ እንደነበር፤ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ማክሰኞ እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። "ሞሐመድ አብዱል ማሊክ ባጃቡ (ISN 10025) ከጓንታናሞ እስር ቤት ለኬንያ መንግሥት እንደተላለፈ የመከላከያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ዛሬ አስታውቋል" ብሏል መግለጫው። የባጃቡ እስር "የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የደህንነት ስጋትን ለመከላከል አስፈላጊ ሆኖ ባለመገኘቱ" ወደ ሀገሩ ለመመለስ ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ መግለጫው አክሎ ገልጿል። በፈረንጆቹ 2007 የታሰረው ኬንያዊው፤ የአልቃይዳ* የምስራቅ አፍሪካ ቅርንጫፍ አባል ነህ ተብሎ እንደተከሰሰ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። *አልቃይዳ በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት በሕገ-ወጥነት የተፈረጀ አሸባሪ ድርጅት ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
አሜሪካ ኬንያዊ የጓንታናሞ እስረኛን ወደ ሀገሩ እንደመለሰች ፔንታጎን አስታወቀ
አሜሪካ ኬንያዊ የጓንታናሞ እስረኛን ወደ ሀገሩ እንደመለሰች ፔንታጎን አስታወቀ
Sputnik አፍሪካ
አሜሪካ ኬንያዊ የጓንታናሞ እስረኛን ወደ ሀገሩ እንደመለሰች ፔንታጎን አስታወቀ ኬንያዊው ሞሐመድ አብዱል ማሊክ ባጃቡ፤ በአስከፊው ጓንታናሞ ቤይ ተቋም ውስጥ ከቀሩት 30 እስረኞች አንዱ እንደነበር፤ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ማክሰኞ እለት... 18.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-18T16:13+0300
2024-12-18T16:13+0300
2024-12-18T16:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий