ኢትዮጵያና ታንዛኒያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና ታንዛኒያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ተስማሙ ሁለቱ ሀገራት ማክሰኞ እለት ባካሄዱት የኢትዮ-ታንዛንያ የጋራ የሚኒስትሮች የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ ነው ስምምነቱን የተፈራረሙት። በስብሰባው ላይ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፤ የኢትዮጵያ እና ታንዛንያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል። የታንዛንያ የውጭ ጉዳይ እና የምስራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማሕሙድ ታቢት ኮምቦ በበኩላቸው ጸጥታ፣ ምጣኔ ሃብት፣ ቱሪዝምና መሰል ዘርፎች በቀጣይ በስፋት በትብብር መስራት የሚቻልባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በኢንዱስትሪ፣ በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በአቪዬሽን፣ ስደትን መከላከል፣ በእንስሳት እርባታና በማቀነባበሪያ ዘርፎች አብሮ ለመሰራት የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0