የኢትዮጵያን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ውድድር የሚከፍት ሕግ በፓርላማ ጸደቀ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያን የባንክ ዘርፍ ለውጭ ውድድር የሚከፍት ሕግ በፓርላማ ጸደቀ የኢትዮጵያ ፓርላማ የምስራቅ አፍሪካዊቷን ሀገር የባንክ ዘርፍ ለውጭ ውድድር ክፍት የሚያደርገውን ሕግ ማክሰኞ እለት ያጸደቀ ሲሆን፤ መንግሥት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ለሚያደረገው ሰፊ ጥረት ቁልፍ እርምጃ ነው። እርምጃው የውጭ ባንኮች ተቀጠላ ኩባንያዎች፣ ቅርንጫፎች ወይም ወኪል ቢሮዎችን እንዲያቋቁሙ እና በሀገር ውስጥ ባንኮች 40% የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖራቸው ያስችላል። ይህም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጀመረው መንግሥት መር ኢኮኖሚውን ነጻ የማድረግ ሂደት ትልቁ አካል ነው። ፓርላማው ህጉን በአብላጫ ድምጽ ቢያፀድቅም፤ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በሀገር ውስጥ ባንኮች ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ተፅዕኖ በማንሳት ስጋታቸውን ገልጸዋል። የማዕከላዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ግን ፉክክር መኖሩ የኢትዮጵያ ባንኮችን ያጠናክራል ሲሉ ተከራክረዋል። ማሻሻያው ኢትዮጵያ በቅርቡ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ድጋፍ ማግኘቷን እና የብር መገበበያዋን ነጻ ማድረጓን ተከትሎ የመጣ ነው። በወለድ ተመን ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ፖሊሲ ​​ተግባራዊ ማድረግ የማሻሻያው አንዱ አካል ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0