የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ለተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት የክብር ሜዳሊያ አበረከተ

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ለተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት የክብር ሜዳሊያ አበረከተ ሽልማቱ የተበረከተው ሰራዊቱ በሶማሊያ ሰላም እና ጸጥታን ለማረጋገጥ ለተጫወተው ጉልህ ሚና መሆኑ ተገልጿል፡፡የአትሚስ የጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ክንዱ ገዙ ሰራዊቱ ላሳየው ቁርጠኝነት፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባር እና የተልዕኮ አፈፃፀም አድናቆታቸውን እንደቸሩ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።ሰራዊቱ ለሶማሊያ ሰላም እና መረጋጋት ለሰራው ስራ እንዲሁም ለከፈለው መስዋዕትነት የክብር ሜዳሊያው እንደተበረከተም ነው ብርጋዴር ጄነራል ክንዱ የገለጹት፡፡ ኢትዮጵያ ከ1950ዎቹ  ጀምሮ ለቀጣናው እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ሰላም የማስከበር ተልዕኮ የድርሻዋን ሚና ስትወጣ ቆይታለች። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0