በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተከስቶ የነበረው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ከባድ የወባ በሽታ ዓይነት መሆኑ እንደተረጋገጠ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ በሽታው የመተንፈሻ አካላትን እንደሚያጠቃ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል። አብዛኞቹ ታማሚዎች በከባድ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አካላዊ ድካም እንደታየባቸውም ሚኒስቴሩ ጠቁሟል። ወረርሽኙ የተከሰተው በኮንጎ ክዋንጎ ክልል ውስጥ ነው። የማይታወቅ እንደሆነ ተገልጾ የነበረው በሽታ ከፍተኛ ትኩሳት እና የራስ ምታት ባህሪ አለው። የዓለም ጤና ድርጅት ባለሙያዎችን ጨምሮ፤ ሳይንቲስቶች ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ የበሽታውን መነሻ እና የመተላለፊያ መንገድ ለማወቅ ሲሞክሩ ቆይተዋል። እንደ ባለስልጣናት ገለጻ አሁን ጥረታቸው በስኬት ተጠናቋል። የኮንጎ መንግሥት ይፋዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በበሽታው በአጠቃላይ 593 ሰዎች የተያዙ ሲሆን፤ 36 ሰዎች ሞተዋል። የክዋንጎ ክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው የ143 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተከስቶ የነበረው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ከባድ የወባ በሽታ ዓይነት መሆኑ እንደተረጋገጠ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተከስቶ የነበረው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ከባድ የወባ በሽታ ዓይነት መሆኑ እንደተረጋገጠ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ
Sputnik አፍሪካ
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተከስቶ የነበረው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ከባድ የወባ በሽታ ዓይነት መሆኑ እንደተረጋገጠ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ በሽታው የመተንፈሻ አካላትን እንደሚያጠቃ የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ጤና ሚኒስቴር... 18.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-18T10:21+0300
2024-12-18T10:21+0300
2024-12-18T10:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተከስቶ የነበረው ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ ከባድ የወባ በሽታ ዓይነት መሆኑ እንደተረጋገጠ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ
10:21 18.12.2024 (የተሻሻለ: 10:44 18.12.2024)
ሰብስክራይብ