"ግዴታዬን ነው የተወጣሁት"፦ የራሱን የሰርግ መልስ ፕሮግራም አቋርጦ የአንዲት ወላድ እናትን ሕይወት ያተረፈው ኢትዮጵያዊ ዶክተር ከሰሞኑ የማኀበራዊ ትስስር ገጾች መነጋገሪያ ሆኗል

ሰብስክራይብ
"ግዴታዬን ነው የተወጣሁት"፦ የራሱን የሰርግ መልስ ፕሮግራም አቋርጦ የአንዲት ወላድ እናትን ሕይወት ያተረፈው ኢትዮጵያዊ ዶክተር ከሰሞኑ የማኀበራዊ ትስስር ገጾች መነጋገሪያ ሆኗል ‍በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ በንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚያገለግለው ዶ/ር በየነ አበራ፣ ከትናንት በስቲያ እሁድ የመልስ ፕሮግራሙን ከቤተ ዘመድ ጋር እያከናወነ ነበር፡፡ የአንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ባለቤት ወደ ዶ/ር በየነ ስልክ አፈላልጎ በመደወል በተሸበረ ድምጽ "ልጄ  ሊታፈን ስለሆነ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት ድረስልን" ይለዋል፡፡ ዶክተር በየነ የመልስ ፕሮግራሙን በመተው ወደ ሕክምና ተቋም በማምራት በምጥ ጭንቅ ላይ የነበረችውን ሴት በሰላም እንድትገላገል አስችሏል፡፡ "በማኀበራዊ ትስስር ገጾች የተዘዋወረው ፎቶ ጉዳዩን መነጋገሪያ አደረገው እንጂ፤ ይሄ የዘወትር ሥራዬ ነው" ሲል በየነ ስለ ድንገተኛ ዝናው በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0