ሞቷል ተብሎ በአስከሬን ክፍል ውስጥ ለአንድ ቀን የቆየ የጋዛ ሕጻን ተአምራዊ በሆነ መንገድ ተረፈ

ሰብስክራይብ
ሞቷል ተብሎ በአስከሬን ክፍል ውስጥ ለአንድ ቀን የቆየ የጋዛ ሕጻን ተአምራዊ በሆነ መንገድ ተረፈ እስራኤል በጋዛ የስደተኞች ካምፕ ላይ ባካሄደችው የአየር ጥቃት ሞሐመድ አል-ዳላሳህ በስህተት ሞቷል ተብሎ ከሌሎች ተጎጂዎች ጋር ወደ አስከሬን ክፍል ተልኳል። አጎቱ የህይወት ምልክቶችን ከማየቱ በፊት 24 ሰዓታትን በአስክሬን ክፍሉ ውስጥ አሳልፏል። በፍጥነት ወደ ሆስፒታል የተወሰደው ሞሐመድ ከ15 ቀን ኮማ በኋላ ሊነቃ ችሏል። "ሞሐመድ በህይወት እንዳለ ሲታወቅ ችግሬን ሁሉ ረሳሁ፤ ምክንያቱም ከቤተሰቦቼ የተረፈ ሰው አግኝቻለሁ" ሲል አጎቱ ለስፑትኒክ ተናግሯል። ሕጻኑ ከባድ የጭንቅላት ጉዳት፣ የራስ ቅል ስብራት፣ አንድ ጆሮውን እንዳጣ እና እግሩ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት አጎቱ ገልጿል። "በሰራተኞች እና በመሳሪያዎች እጥረት፣ ከጥቃተት በኋላ በሚፈጠር መጨናነቅ ምክንያት ይዋል ይደር እንጂ አንዳንድ ስህተቶች መከሰታቸው የማይቀር ነው" ብለዋል ዶክተር አህድ ኻላፍ። በተጣለው እገዳ ምክንያት ከባድ የሕክምና ባለሙያዎች እና መሳሪያዎች እጥረት ሁኔታውን እንዳባባሰ ዶክተሩ ተናግረዋል። ተግዳሮቶቹን ለመቅረፍ ለህክምና አቅርቦቶች እና የኤሌክትሪክ እጥረት መፍትሄ መስጠትን ጨምሮ የውጭ እርዳታ እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል። "እሱ (ሞሐመድ አል-ደአላህ) ሁሉንም ነገር ያስታውሳል። የሮኬት ድምፅ ሲሰማ መንቀጥቀጥ ይጀምራል። 'አለሁልህ፣ ምንም አትሆንም' ስለው ብቻ ነው እንቅልፍ የሚወስደው። ይህን የተረገመ ጦርነት አቁሙ። ሰዎች ወደ ቤታቸው ይመለሱበት" ሲል የሕጻኑ አጎት ተናግሯል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0