የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶአን በቅርቡ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን እንደሚጎበኙ ገለጹ

ሰብስክራይብ
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶአን በቅርቡ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን እንደሚጎበኙ ገለጹ ኤርዶአን በፈረንጆቹ 2025 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት ሁለቱን ሀገራት ለመጎብኘት ማቀዳቸውን የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ጉብኝቱ በኢትዮጵያና ሶማሊያ መኻከል ተፈጥሮ የነበረው ውጥረት በፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶአን አደራዳሪነት መርገቡን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ የአንካራው ስምምነት ሰባት ሰዓታት ከቆየ ውይይት በኋላ ሊደረስ እንደቻለ የገለጹት የቱርኩ መሪ፤ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጋር ያላት ጥሩ ግኑኝነት ለስምምነቱ መሳካት ቁልፍ እንደነበር ጠቁመዋል። "በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መኻከል ያለው ችግር ለብዙ ዓመታት የቆየ ነው። ኢትዮጵያ ግዙፍ ናት፣ ከሶማሊያ በሁለት እጥፍ ብትበልጥም ወደብ አልባ ነች" ብለዋል። ኤርዶአን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር መልካም ግኑኝነት እንዳላቸውም ያነሱ ሲሆን፤ ይህም በጠቡ ዙርያ ለመወያያት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል። "እንዲህ ያለ ትልቅና ግዙፍ መሬት ወደብ አልባ መሆኑ በእጅጉ ይረብሻቸዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ሀገራት ቢሳተፉም ችግሩን ግን መፍታት አልቻሉም" ሲሉም አክለዋል።በአንካራው ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ አንዳቸው ያንዳቸውን ሉዓላዊነት፣ አንድነት፣ ነጻነት እና የግዛት አንድነት እንደሚያከብሩ አረጋግጠዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0