የሱዳን አማፂ ቡድን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሰሜን ዳርፉር በሚገኝ ሆስፒታል ላይ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ

ሰብስክራይብ
የሱዳን አማፂ ቡድን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሰሜን ዳርፉር በሚገኝ ሆስፒታል ላይ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ሰሜን ዳርፉር በሚገኘው አል-ፋሺር ሆስፒታል ላይ አርብ እለት በድሮን ሚሳኤልም ጭምር ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂ እንደሆነ ተገልጿል። በጥቃቱ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ ሃያ የሚሆኑ የቆሰሉ ሲሆን፤ በሆስፒታል ክፍሎችና በሌሎች ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው የጤና ባለስልጣናት እና የሲቪል ተሟጋቾች ተናግረዋል። በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እና በሱዳን ጦር መካከል ላለፉት 20 ወራት የዘለቀው ግጭት፤ ከ12 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አፈናቅሎ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ መፍጠሩን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ያሳያል። አርኤስኤፍ ቁልፍ የጦር አውድማ በሆነው አል-ፋሺር ድል የሚያደርግ ከሆነ፤ ባለፈው  ዓመት በምዕራብ ዳርፉር የተፈጸመው የጎሳ ጥቃት ይደገማል የሚል ስጋት እንዳለ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ የረሃብ ችግር የተደቀነባቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሚጠለሉበት ዛምዛም የስደተኞች ካምፕ ላይ የሚያካሂዳቸው ጥቃቶች ሁኔታውን የበለጠ አባብሶታል ተብሏል። አርኤስኤፍ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ባካሄደው የመድፍ ጥቃት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በተባበሩት መንግሥታት ከሚመራው ካምፕ እንዲሸሹ ተገደዋል። የሱዳን ጦር በአካባቢው በሚገኙ የአርኤስኤፍ ይዞታዎች ላይ ባነጣጠረ የአየር ጥቃት ምላሽ እንደሰጠ ተገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0