የቀድሞው የሞሪሸስ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ በማጭበርበር ወንጀል ምርመራ ተከፈተባቸው

ሰብስክራይብ
የቀድሞው የሞሪሸስ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ በማጭበርበር ወንጀል ምርመራ ተከፈተባቸው የሞሪሸስ ፖሊስ በአሁኑ ጊዜ ከሀገር ውጭ ናቸው የተባሉት የቀድሞ የማዕከላዊ ባንክ ገዥ ሃርቬሽ ኩማር ሴጎላም ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። የእስር ማዘዣው የገንዘብ ብዝበዛን አስመልክቶ የተከፈተው ምርመራ አካል ነው። የክሱ ዝርዝር ጉዳዮች አልተገለፁም። በቅርቡ በፓርላማ ይፋ የተደረገ ሪፖርት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ ለመቋቋም በ2020 የተቋቋመውን የሞሪሸስ ኢንቨስትመንት ኮርፖሬሽን ለመደገፍ፤ በሕገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ አትሟል ሲል የሞሪሸስ ማዕከላዊ ባንክ ላይ ክስ አቅርቧል። ባንኩ ይፋ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከመጠቀም ይልቅ፤ ገንዘብ በማተሙ ምክንያት በገንዘብ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ለዋጋ ንረትና ለሀገሪቱ መገበያያ አለመረጋጋት አስተዋጽኦ አድርጓል ተብሏል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0