ተመራጩ የጋና ፕሬዝዳንት የአይኤምኤፍን የድጋፍ ስምምነት እንደሚገመግሙ ጠቆሙ

ሰብስክራይብ
ተመራጩ የጋና ፕሬዝዳንት የአይኤምኤፍን የድጋፍ ስምምነት እንደሚገመግሙ ጠቆሙ አዲስ የተመረጡት የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ሀገሪቱ ከአይኤምኤፍ ጋር የገባችውን የ3 ቢሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት እንደሚያከብሩ ያስታወቁ ሲሆን፤ አስፈላጊው ማስተካከያ መደረግ አለበት ብለው እንደሚያምኑ ግን ግልፅ አድርገዋል። በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ወሳኝ ድል ያስመዘገቡት ማሃማ ለምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለምልልስ "በድጋሚ ስለመደራደር ሳወራ ፕሮግራሙን እንተዋለን ማለቴ አይደለም" ብለዋል። "በስምምነቱ እንገዛለን ሆኖም መሬት ካለው እውነታ ጋር የሚጣጣሙ አንዳንድ ማስተካከያዎችን ማድረግ መቻል አለበት።" አስተዳደራቸው የመንግሥት ወጪ ብክነትን ለመቀነስ እና በኢነርጂ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት አቅዷል። ከአስርት ዓመታት በኋላ መጥፎ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የምትገኘውን ሀገር የተረከቡት ማሃማ፤ የዋጋ ግሽበት እና የምንዛሪ ዋጋ ማሽቆልቆልንም ለመቅረፍ አስበዋል። "የኢኮኖሚው ሁኔታ አስከፊ ነው ...ነፍሴን፣ አካሌን እና ሁሉንም ነገሬን በመስጠት የጋናውያንን ህይወት ማሻሻል ላይ አተኩራለሁ" ያሉት ማሃማ የአይኤምኤፍ ፕሮግራም አካል የሆነውን "የታክስ ብዛት" የንግድ እድገትን የሚያግድ ነው በማለት ተችተዋል። ወጪ ቅነሳን በተመለከተ መንግሥት ላይ በቂ ጫና እየተደረገ አይደለም ያሉት ፖለቲከኛው፤ ከፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት በመጀመር የወጪ ቅነሳ ፕሮግራሙን በድጋሚ እንደሚገመግሙ ገልጸዋል። “ፕሬዝዳንቱ ቀበቶአችንን እንድናጠብቅ የሚጠይቅ ከሆነ፤ እርሱም ቀበቶውን ማጥበቅ ይኖርበታል” ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0