ኢትዮጵያና ኡጋንዳ ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተሥማሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና ኡጋንዳ ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተሥማሙ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኡጋንዳ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙሖዚ ኬንሩጋባ በወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት አካሂደዋል። በመረጃ፣ በወታደራዊ ኢንዱስትሪ፣ በስልጠና እና መሰል ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በተለይም ከስደተኞች ጋር በመመሸግ ወንጀል የሚፈፅሙ አካላትን ለመለዋወጥ፤ ከስምምነት ላይ እንደደረሱ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ በኡጋንዳ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙሆዚ ኬንሩጋባ ለተመራው የልዑካን ቡድን ስጦታዎችንም አበርክተዋል። ምስሎቹ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኙ ናቸው። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0