በሱማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ከኢትዩጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት በመልካም ተቀበለውበቱርክ አሸማጋይነት የተካሄደው የሞቃዲሾ እና የአዲስ አበባ የሰላም ስምምነት ምሳሌነት ያለው ለክልሉ ሰላም ወሳኝ ሚና ያለው ነው በማለት ሞሀሐድ አል አሚን ሱዩፍ የአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ኮሚሽን ሊቀመንበር ልዩ መልክተኛ እና የአፍሪካ ህብረት የሱማሊያ ሽግግር ቢሮ (አትሚስ) ሀላፊ ተናግረዋል። " አትሚስ የሱማሊያን የሀገር-ግንባታ እና የፀጥታ ሽግግር በትጋት ለመደገፍ ዝግጁ ነው ፤ ይህም ከሱማሊያ ህዝቦች ፍላጎት እና የተረጋጋች እና የበለፀገች አፍሪካን እንድትፈጠር አላማ ካለው የአፍሪካ ህብረት አላማ ጋር አብሮ የሚሄድ ነው" በማለት ሱዩፍ ሁለቱም ሀገራት የተስማሙበትን እንዲተገብሩ እና የጋራ ትብብራቸውን እንዳያጠነክሩ በማለት በመግለጫቸው ጥሪ አቅርበዋል። በኢትዩጵያ እና በሱማሊያ መካከል ውጥረት የነገሰው ከሱማልያ የተገነጠለችው ሱማሌላንድ ኢትዩጵያ በቀይ ባህር ላይ የባህር በር እንድታገኝ በምትኩ ሱማሊላንድ የነፃ ሀገርነት እውቅናን ከኢትዮጵያ እንድታገኝ የተፈራረሙት ስምምነት በሱማሊያ በኩል ውግዘት ገጥሞት በነበረበት ወቅት ነው።በአንካራ በተፈረመው የጋራ ስምምነት ወቅት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ እና የሱማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ከሁለቱም ሀገራት የሚጠበቀውን ሉአላዊነት ፣ አንድነት ፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት ለማክበር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያረጋገጡ ሲሆን ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ የሚረዳትን ስምምነት ስራዎች በጋራ ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በሱማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ከኢትዩጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት በመልካም ተቀበለው
በሱማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ከኢትዩጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት በመልካም ተቀበለው
Sputnik አፍሪካ
በሱማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ከኢትዩጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት በመልካም ተቀበለውበቱርክ አሸማጋይነት የተካሄደው የሞቃዲሾ እና የአዲስ አበባ የሰላም ስምምነት ምሳሌነት ያለው ለክልሉ ሰላም ወሳኝ ሚና ያለው ነው በማለት ሞሀሐድ አል... 14.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-14T12:53+0300
2024-12-14T12:53+0300
2024-12-14T13:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በሱማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ተልእኮ ከኢትዩጵያ ጋር የተደረገውን ስምምነት በመልካም ተቀበለው
12:53 14.12.2024 (የተሻሻለ: 13:14 14.12.2024)
ሰብስክራይብ