የሩሲያ የሰብዓዊ ደህንነት ተቆጣጣሪ ድርጅት የሆነው ሮስፖትሬብናድዞር እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአፍሪካን ሀገራት ጨምሮ ወደ ሰባት ሀገራት ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪዎችን ሊልክ ነው

ሰብስክራይብ
የሩሲያ የሰብዓዊ ደህንነት ተቆጣጣሪ ድርጅት የሆነው ሮስፖትሬብናድዞር እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአፍሪካን ሀገራት ጨምሮ ወደ ሰባት ሀገራት ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪዎችን ሊልክ ነው "በዘመናዊ መሳሪያዎች የተሞሉና የተለያያ አይነት ያላቸው ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪዎቹ ራቅ ባሉ አካባቢዎች ምርመራ ለማድረግ፣ በበሽታው የተጠቁ አካባቢዎች ክትትል ለማድረግ እና በቡድን በሽታ በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ምርምር ለማድረግ ይረዳሉ። በ24 ሰዓታት ውስጥ በሩሲያም ሆነ በዓለም ላይ በየትኛውም ቦታ ሊተላለፉ ይችላሉ” ሲሉ የሮስፖትሬብናድዞር ኃላፊ ኣና ፖፖቫ ገልጸዋል።ኃላፊዋ አክለውም ሩሲያ ከጎርጎሮሳውያኑ 2015 ጀምሮ ላቦራቶሪዎችን ለዓለም አቀፍ አጋሮች እያቀረበች እንደነበረ እና እስከዛሬም 35 ተንቀሳቃሽ ፀረ-ወረርሽኝ ላቦራቶሪዎች እጅግ በሚፈለጉበት 14 ሀገሮች ውስጥ ግልጋሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውሰዋል። ፖፖቫ ተንቀሳቃሽ ላቦራቶሪዎች ወደ ኢትዮጵያ፣ ቬትናም፣ ሞንጎሊያ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ እና ማዳጋስካር እንዲሁም በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ ላቦራቶሪዎች ደግሞ ወደ ካዛክስታን እና ቤላሩስ እንደሚላኩ ገልፀዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0