አየርላንድ በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ የከፈተውን ክስ ልትቀላቀል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገለጹ

ሰብስክራይብ
አየርላንድ በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ የከፈተውን ክስ ልትቀላቀል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ገለጹ“የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክል ማርቲን መንግስት ደቡብ አፍሪካ በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ የከፈተችውን የዘር ማጥፋት ክስ አየርላንድ እንደትቀላቀል ፍቃድ መስጠቱን በዛሬው ዕለት ገልጸዋል። በክሱ መቀላቀሏን በተመለከተ በተያዘው ወር በሄግ ፍርድ ቤት ህጋዊ ሰነድ ታስገባለች” ሲል የአየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ገልጿል።ማርቲን፤ አየርላንድ ፍርድ ቤቱን "በሀገሪቱ ዘር ማጥፋት መፈፀሙን የሚያመላክት ትርጓሜውን" እንዲያሰፋ ትጠይቃለች በማለታቸው በመግለጫው ተጠቅሷል።"የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን የሚያመላክቱ ትርጓሜዎች በጣም መጥበብ ያሳስበናል፤ ይህም የሲቪሎች ጥበቃን በማጥበብ ያለመቀጣት ባህልን ያስከትላል” ሲሉ አክለዋል። ደቡብ አፍሪካ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በታህሳስ 2023 እስራኤል በጋዛ በምታካሄደው ጦርነት ምክንያት የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ጊዜያዊ እርምጃ እንዲወስድ ክስ መስርታለች። ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በፍልስጤም ላይ እየወሰደች ያለው እርምጃ "ዘር ማጥፋትን በተመለከተ የተደረገ ስምምነት ስር የተደነገጉት ግዴታዎች የሚጥስ ነው" ብላለች።በጎርጎሮሳውያኑ ጥር ወር በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳትፈጽም፣ በፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲፈፀም ማነሳሳትን እንድትቀጣ እና የሰብአዊ እርዳታ መተላለፍ እንዲረጋገጥ ትዕዛዝ ሰጥቷል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0