የአፍሪካ ሀገሮች በቅርብ በተመድ ፀጥታው ምክርቤት ቋሚ መቀመጫ ይኖራቸዋል በማለት የተመድ ዋና ፀሀፊ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
 የአፍሪካ ሀገሮች በቅርብ በተመድ ፀጥታው ምክርቤት ቋሚ መቀመጫ ይኖራቸዋል በማለት የተመድ ዋና ፀሀፊ ተናገሩ " የአፍሪካ ሀገራት በተመድ ፀጥታ ምክርቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራቸው ከፍተኛ መሰናክል ሲፈጥር የነበረው ተሸንፏል። ሁለት የአፍሪካ ሀገራት በፀጥታው ምክርቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራቸው መግባባት ላይ ተደርሷል። እኔ እርግጠኛ  በተመድ ያለኝን ዋና ፀሀፊነት የአፍሪካ ሀገሮች በፀጥታው ምክርቤት ቋሚ መቀመጫ ማግኘታቸውን ሳላይ እንደማለቅ" በማለት አንቶኒዩ ጉተሬዝ በፕሪቶሪያ በነበራቸው ይፋዊ ጉብኝት ወቅት ለሪፖርተሮች ተናግረዋል። ጉተሬዝ አክለውም የደቡቡ አለም ተፅእኖ በተመድ ስራ ላይ ወሳኝ ነው ብለዋል። " የደቡብ አለም ሀገራት አብዛኛውን የአለም ህዝብ ይወክላሉ። ወሳኝ የሆነ ተፅዕኖ በተመድ ስራዎች ላይ ያሳድራሉ" በማለት ፀሀፊው በአፅንኦት ተናግረዋል።አፍሪካ በተመድ ቋሚ  ፀጥታ ምክርቤት ውስጥ ያለ ምንም ተወካይ መቆየቷ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት ጉተሬዝ ለሚዲያዎች ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0