ኢትዩጵያ እና ሱማሊያ በሀገራቱን የጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ልማት እና ሰላም ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸው ስምምነት ተፈራረሙሀገራቱ በመሀካለቸው ያለውን አለመስማማት በመቋጨት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ልማት እንዲሁም ሰላም ላይ አብሮ ለመስራት በቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይቡ ኤርዶዋን አሸማጋይነት ተፈራርመዋል። በስምምነት ፊርማው ወቅት ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ሀገራቱ የኋላውን ትተዉ በወደፊቱ ላይ አተኩረው ስለመፈራረማቸው " እና እነዚህ ሁለት ቤተሰብ የሆኑ ሀገሮች ለኛ ጠቃሚ የሆኑ ከአሁን በኋላ ስለሚገነቡት መርህ አሁን ተመዝግቧል" በማለት በፊርማው ስነስርአት ወቅት ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም " የክልሉ ህዝቦች ተግዳሮቶችን በብልሀት የማሸነፍ ታሪክ አላቸው። በዚህ የጋራ መግለጫ ትብብርን ለማጠናከር ፣ የኢኮኖሚ ልማትንና ብልፅግናን ለማምጣት ይሄ ጠንካራ መሰረት ይሆናል" ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስተር ዓብይ አህመድ በበኩላቸው " እንደ ጎረቤት ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ ለዘመናት የቆየ ግንኙነት አላቸው። ጎረቤት ብቻ አይደለንም እጣፈንታቸው በደም የተሳሰረ እህት እና ወንድም ጭምር እንጂ። ኢትዩጵያን እና ሱማሊያ የጋራ የዘር ግንድ ፣ ቋንቋ እና ባህል ብቻ ሳይሆን በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዩጵያ ወታደሮች ሀገሪቷን ፀጥታ ለማስከበር ከአሸባሪዎች ጋር በነበራቸው ትንቅንቅ በከፈሉት የደም መስዋትነት ተሳስረዋል" "ሱማሊያ የኢትዮጵያ እውነተኛ ጓደኛ ነበረች አሁንም መሆኗን ለመጪዎቹ አመታትም ጭምር ትቀጥላለች። በዚህ ግንኙነት መሰረት ህዝባችንን ተጠቃሚ ይሆናል። እኛ ሰላም እና መረጋጋት የህዝባችን ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖ የሚያስፈልግበት ክልል ውስጥ ነው ያለነው" በማለት የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም "እዚህ እንዳልነው በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከአመታት በፊት ለከፈሉት መስዋትነት እውቅና እንሰጣለን ፤ ይህም ህዝቦቻችን ምን ያህል እርስበርስ እንደተዛመዱ ያሳይል የሚቀጥልም ይሆናል" በማለት እንደተናገሩ ፋና ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኢትዩጵያ እና ሱማሊያ በሀገራቱን የጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ልማት እና ሰላም ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸው ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዩጵያ እና ሱማሊያ በሀገራቱን የጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ልማት እና ሰላም ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸው ስምምነት ተፈራረሙ
Sputnik አፍሪካ
ኢትዩጵያ እና ሱማሊያ በሀገራቱን የጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ልማት እና ሰላም ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸው ስምምነት ተፈራረሙሀገራቱ በመሀካለቸው ያለውን አለመስማማት በመቋጨት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ልማት እንዲሁም ሰላም ላይ አብሮ ለመስራት... 12.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-12T12:10+0300
2024-12-12T12:10+0300
2024-12-12T12:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኢትዩጵያ እና ሱማሊያ በሀገራቱን የጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ልማት እና ሰላም ላይ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸው ስምምነት ተፈራረሙ
12:10 12.12.2024 (የተሻሻለ: 12:44 12.12.2024)
ሰብስክራይብ