ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በዲጂታል ግብር ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ያላቸውን አጋርነት ለማሳደግ ተስማሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በዲጂታል ግብር ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ያላቸውን አጋርነት ለማሳደግ ተስማሙ የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒሰትር እና የሩሲያ ፌደራል ግብር አገልግሎት በዲጂታል ግብር ትራንስፎርሜሽን ዙሪያ ያላቸውን ስምምነት ለማሳደግ የሚረዳ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ። ይህ ስትራቴጂክ አጋርነት የተሻለ የግብር መሰብሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም ኢትዮጵያ የተሻለ የሀገር ውስጥ ገቢ እንዲኖራት ያደርጋል። የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነት ውስጥ የምታደርገውን ጥረት ኢኮኖሚያዊ እድሎች፣ የሀገሪቱን ጥቅም መጨመር እና የልማት ተግዳሮቶችን መጋፈጥ ጥረቶች አንዱ ማሳያ ነው በማለት በአፅንኦት ተናግረዋል። የሩሲያ ፌደራል ግብር አገልግሎት አለምአቀፍ  ትብብር ዳይሮክተሬት ዋና ሀላፊ የሆኑት ኤልሴይ ባልታ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የገቢ አሰባሰብ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መነሳቷን አበረታተው ፤ ይህ የሀገር ውስጥ ገቢ አስፈላጊ እና የመንግስት የጀርባ አጥንት መሆኑን አስታውሰዋል። አክለውም ሀገራቸው በዲጂታል ግብር ትራንሰፎርሜሽን ዘርፍ ያላትን ልምድ በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማገዝ ፍቃደኛ መሆንዋን ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0