ለአረቢካ ቡና የሚሰጠው የዋጋ መጠን በ4 በመቶ በላይ በማደግ ከ7500 ዶላር በላይ በቶን ተተመነ

ሰብስክራይብ
ለአረቢካ ቡና የሚሰጠው የዋጋ መጠን በ4 በመቶ በላይ በማደግ ከ7500 ዶላር በላይ በቶን ተተመነ ይህ በትላንትናው ገበያ የተመዘገበዉ ዋጋ ከጎርጎሮሳውያኑ ሚያዚያ 1977 በኋላ አዲስ ሪከርድ ነው። አረቢካ የተሰኘው የቡና ዝርያ ካለፈው ሚያዚያ ወር ጀምሮ በአለም የቡና ገበያ በየወሩ የዋጋ ጭማሪ እያደረገ ይገኛል። ከጎርጎሮሳውያኑ መስከረም 2011 በኋላ ባለፈዉ መስከረም ዋጋው 6000 ዶላር በቶን ደርሶ ነበር። ባለፈው ህዳር ዋጋው 30 በመቶ ሲጨምር የታህሳስ ወር ከገባ ጀምሮ በ8 በመቶ ተጨማሪ ጭማሪ አሳይቷል። የአረቢካ እና ሮቡስታ ቡና ከፍተኛ ነጋዴ የሆነው ቮልካፌ ሊሚትድ በብራዚል ካደረገው የምርት ጉብኝት በኋላ ለአረቢካ ቡና ምርት ያስቀመጠውን ቅድመ ግመታ ዝቅ ማድረጉን ብሉምበርግ ዘግቧል። የአለም ትልቋ ጥሬ ቡና አምራች የሆነችው ብራዚል ለቡና ምርቷ ተስማሚ ያልሆነ የአየር ሁኔታ በቅድሚያ ድርቅ ፣ ሙቀት እና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በቡና ምርቱ ማበቢያ እና እድገት ወቅት እንደገጠማት ተነግሯል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0