ቱርክ የኢትዩጵያን እና የሱማሊያን መሪዎች ንግግር ለማስተናገድ አቅዳለችአንካራ እንዳለችው ይህ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዓብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ መካከል በቀጥታ የሚደረገው ንግግር በሀገራቱ መካከል ያለውን ልዩነት የማጥበብ አለማ ያለው ነው። የሱማሊያ ሚዲያዎች ፕሬዝዳንት ሞሀመድ በቱርክ ጉብኝታቸው ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዓብይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩ ሲዘግቡ ፤ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ አስተያየት ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን በተመሳሳይ በቱርክ የኢትዩጵያን ኤምባሲ ሀሳብ አልሰጥበትም ብሏል። በጎርጎሮሳዊያኑ 2024 መጀመሪያ ነበር የኢትዮጵያ መንግስት ከራስ ገዟ ሱማሌላንድ ጋር የባህር በር ለማግኘት ይረዳኛል ያለውን ስምምነት የተፈራረመው። ስምምነቱን ሱማሌላንድ ግዛቴ ናት የምትለው ሱማሊያ ሉአላዊነቴን ይጋፋል በማለት እየተቃወመችው ነው።ይህ ውጥረት በነገሰበት ወቅት የቱርክ መንግስት የሱማሊያን ባህር ሀይል ማቋቋምን ጨምሮ ጠንካራ የፀጥታ እና የፖለቲካ አጋርነት ስምምነት ከሱማሊያ መንግስት ጋር ተፈራርመዋል። በዚህ አመት መጀመሪያ ቱርክ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የተካሄደ ውይይት በቱርክ አስተናጋጅነት ተካሄዶ ነበር። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ቱርክ የኢትዩጵያን እና የሱማሊያን መሪዎች ንግግር ለማስተናገድ አቅዳለች
ቱርክ የኢትዩጵያን እና የሱማሊያን መሪዎች ንግግር ለማስተናገድ አቅዳለች
Sputnik አፍሪካ
ቱርክ የኢትዩጵያን እና የሱማሊያን መሪዎች ንግግር ለማስተናገድ አቅዳለችአንካራ እንዳለችው ይህ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዓብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ መካከል በቀጥታ የሚደረገው ንግግር በሀገራቱ መካከል ያለውን ልዩነት የማጥበብ አለማ ያለው... 11.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-11T15:05+0300
2024-12-11T15:05+0300
2024-12-11T15:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий