የታህሳስ 2 ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የታህሳስ 2 ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦ የዛምቢያ ህገመንግስት ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ ለሁለት የስልጣን ዘመናት በፕሬዚዳንትነት መቆየታቸውን በመግለጽ በፕሬዚዳንትነት መቀጠል እንደማይችሉ ወስኗል፤ ኤድጋር ፕሬዚዳንት ሚካኤል ሳታ በጎርጎሮሳውያኑ 2015 መሞታቸውን ተከትሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥልጣን የያዙ ሲሆን በ2021 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም በዩናይትድ ፓርቲ ፎር ናሽናል ዲቭሎፕማንት እጩ በሆኑት ሃካይንዴ ሂቺሌማ ተሸንፈዋል። ከሱዳን መዲና ካርቱም በስተ ምዕራብ በምትገኘው ኦምዱርማን ከተማ በፈጥኖ ደራሽ ኃይል (ራኤስፍ) በተፈጸመው ጥቃት ከ65 በላይ ሰዎችን ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸውን የሱዳን ባለሥልጣናት ገልጸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ የተከሰተውን ያልታወቀ በሽታ መመርመሩን ቀጥሏል። በሀገሪቱ በተከሰተው ያልታወቀ በሽታ የተያዙ አስር ታካሚዎች ላይ በተደረገ ምርመራ በወባ በሽታ መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ተናግረዋል። የሩሲያ የአየር መከላከያ ኃይሎች 14 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በብራያንስክ ክልል ላይ ማውደማቸውንና ማክሸፋቸውን መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። ትራምፕ በዩክሬን ያለውን ግጭት መፍታት ቅድሚያ እንደሚሰጡት ተናግረዋል። ኬቭ የአሜሪካ እርዳታ ከተቋረጠ እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2025 መንፈቅ ያህል የሚቆይ በቂ ገንዘብ፣ የጦር መሳሪያና ጥይቶች ይኖራት ሲሉ የዩክሬን የፋይናንስ ሚኒስትር ማርቼንኮ ገልጸዋል። ደማስቆ በአንፃራዊነት ተረጋግታለች፣ ምንም አይነት ስጋት የለም፣ በርካታ ሱቆችና ካፌዎች እየሰሩ ናቸው፣ አብዛኛው ህዝብ የሶሪያን ዋና ከተማ ለቆ ላለመውጣት ወስኗል ሲሉ ነዋሪ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። የደቡብ ኮሪያ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ኪም ዮንግ-ዩን ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ ማድረጋቸውን ዮንሃፕ የዜና ወኪል ዘግቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0