የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ የአደጋ ስራዎች ማእከል ያልታወቀዉን በሽታ በመመርመር ላይ መሆኑን እና አሁን ላይ በሽታው በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘገበ

ሰብስክራይብ
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ የአደጋ ስራዎች ማእከል ያልታወቀዉን በሽታ በመመርመር ላይ መሆኑን እና አሁን ላይ በሽታው በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘገበ" የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ በሽታዎች ማእከል (ኩስፕ) የበሽታውን መከሰት እንደሰማ ከኢፕዲሞሎጂስቶች (የወረርሺኝ ስፔሻሊስቶች) ፣ ስነ-ህይወት ተመራማሪዎች ፣ የህክምና ባለሙያዎች እና የተላላፊ በሽታዎች መከላከል መቆጣጠር ባለሙያዎች የተወጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው ልኳል" በማለት የኩስፕ አስተባባሪ የሆኑት ክርስቲያን ንጋንዱ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ መናገራቸው ተዘግቧል። እንደ አስተባባሪው ገለፃ ምስጋና ለጤና ባለሙያዎች ይሁን  እና በሽታው ሁኔታ አሁን ላይ የተረጋጋ ነው። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ኩዋንጎ ግዛት ፓንዚ ጤና ክልል ውስጥ ባልታወቀዉ ህመም የሟቾቹ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ በበሽታው ላይ ምርምራ  እንዲከፈት ማድረጉን የሀገር ውስጥ ሚዲያው ጨምሮ ዘግቧል። ባለሙያዎቹ  ከግዛቲቱ እና ከአካባቢው የተወጣጡ ቡድኖች ጋር በመሆን  ኢፕዲሞሎጂ እና ስነ-ህይወት ምርመራዎችን እያጠናከሩ በበሽታው ለተጠቁ ህመምተኞች አስፈላጊውን እንክብካቤ እየሰጡ እንዲሁም ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጥበቃ እያደረጉ መሆኑን ንጋንዱ ተናግሯል ፤ ጨምሮ በግዛቲቱ የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር የትብብር ስብሰባዎችን አስፈላጊነት አፅንኦት ሰጥቶ አብራርቷል።እንደ የአለም የጤና ድርጅት ሪፖርት በጎርጎሮሳዊያኑ ከጥቅምት 24 እስከ ታህሳስ 5  2024 ድረስ 406 ምንነቱ ያልታወቀዉ በሽታ ህመምተኞች በክዋንጎ ግዛት ፓንዚ ጤና ዞን የተመዘገበ ሲሆን የሟቾቹ ቁጥር 31 ደርሷል። የበሽታዉ አብዛኛው ተጠቂዎች ከአምስት አመት በታች ያሉ ጨቅላ ህፃናት ናቸዉ ። ራስምታት ፣ ትኩሳት የመተንፈስ ችግር እና የደም ማነስ ከበሽታው ምልክቶች መሀከል ይካተታሉ ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0