የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የደረሰባቸውን የጭንቅላት ደም መፍሰስ ለማስቆም ድንገተኛ ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው እና በአሁኑ ወቅት በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ተገለጸ

ሰብስክራይብ
የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ የደረሰባቸውን የጭንቅላት ደም መፍሰስ ለማስቆም ድንገተኛ ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው እና በአሁኑ ወቅት በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ተገለጸ ሉላ "መደበኛ" የሆነ የደም ማስወጣት ቀዶ ጥገና ከተደረገላቸው በኋላ፤ በሳኦ ፓውሎ ሆስፒታል ጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ በማገገም ላይ እንደሚገኙ፤ በፕሬዝዳንቱ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተጋራው የሆስፒታል መግለጫ አመልክቷል። የ79 ዓመቱ ሉላ፤ በራስ ህመም ምክንያት ሰኞ አመሻሽ ላይ ብራዚሊያ በሚገኘው ሲሪዮ-ሊባኒስ ሆስፒታል ገብተዋል። የተደረገላቸው የኤምአርአይ (MRI) ምርመራ የጭንቅላት ደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው አሳይቷል። እንደ መግለጫው ማብራሪያ ከሆነ ምርመራውን ተከትሎ፤ ለቀዶ ጥገና ህክምና ወደ ሳኦ ፓውሎ ሲሪዮ-ሊባኒስ ሆስፒታል ተወስደዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0