ኬንያ የግራሚ ሽልማትን ለማዘጋጀት 3.

ሰብስክራይብ
ኬንያ የግራሚ ሽልማትን ለማዘጋጀት 3.9 ሚሊዮን ዶላር የጨረታ ዋጋ አቀረበች ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በሁለተኛ ዓመት የሀስትለር ክብረ በዓል ላይ በኬንያታ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ባደረጉት ንግግር፤ አስተዳደራቸው ኬንያን ወደ ዓለም አቀፍ የመዝናኛ መናሀሪያነት ለመቀየር በትጋት እንደሚሰራ ጠቁመዋል። ይህም ኬንያ በሚያዚያ ወር ከዓለም አቀፉ የግራሚ ማህበር ጋር ለመተባበር ከተመረጡ አራት ሀገራት አንዷ መሆኗን ተከትሎ የመጣ ሲሆን፤ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የፈጠራ ኢንዱስትሪ ያላትን አሻራ ለማጠናከር ያለመ ነው። ፕሬዝዳንት ሩቶ ጥበባትን ከትምህርት ጋር በማዋሃድ፣ ለሥነ ጥበብ አስተማሪዎች ልዩ ሥልጠና መስጠት እና የፈጠራ ኢኮኖሚ ዲፓርትመንት የመሰሉ ተነሳሽነቶችን በማስፋት፤ የሀገር ውስጥ ተሰጥኦዎችን መደገፍ እና ገቢ መፍጠርን አጽንኦት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ከሆሊዉድ ጋር የሚደረጉ ትብብሮች የኬንያን የፊልም ዘርፍ እንደሚያሳድግ እና ለሀገር ውስጥ ፈጠራዎች ዓለም አቀፍ እድሎችን እንደሚከፍት ይጠበቃል። የፕሬዝዳንቱ የልዩ ፕሮጄክቶች እና የፈጠራ ኢኮኖሚ ኃላፊ ዴኒስ ኢቱምቢ፤ በ2027 የዓለም የፈጠራ ኢኮኖሚ ኮንፈረንስ ለማስተናገድ መታቀዱን የገለጹ ሲሆን፤ ኬንያ ዝግጅቱን በማሰናዳት የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0