የቀድሞው የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ በሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አሸናፊ መሆናቸው ተረጋገጠ

ሰብስክራይብ
የቀድሞው የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ በሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አሸናፊ መሆናቸው ተረጋገጠ የምርጫ ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዣን ሜንሳ "የ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኦፊሰር እንደመሆኔ የተከበሩ ጆን ድራማኒ ማሃማ በ56.55% ድምር ድምጽ የ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ እና የጋና ሪፐብሊክ ተመራጭ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን ስገልጽ በታላቅ ክብር ነው" ብለዋል። 12 የሚደርሱ እጩዎች ለጋና ከፍተኛ ሃላፊነት የተወዳደሩ ሲሆን፤ የሁለቱ ተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች የተቃዋሚው ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ኮንግረስ ማሃማ እና የገዥው አዲሱ የአርበኞች ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ማሃሙዱ ባውሚያ ዋና ተፎካካሪ ነበሩ። ሁለተኛውን እና የመጨረሻውን የስልጣን ዘመናቸውን እያገለገሉ የሚገኙት የገዥው የአዲሱ የአርበኞች ፓርቲ መሪ ፕሬዝደንት ናና አኩፎ-አዶ በውድድሩ ለመሳተፍ ብቁ አልነበሩም። በምርጫው መሸነፋቸውን የተቀበሉት ባዉሚያ፤ ለማሃማ ድል የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት እንዳስተላለፉ የጋናዌብ የዜና ፖርታል ዘግቧል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0