የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የእስራኤል ጦር በጋዛ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አውግዘው፤ "አረመኔያዊ ያሉት ጦርነት" እንዲቆም ጠየቁ "እንደ ሀገር የመሬቶቻችን በቅኝ ግዛት ስር መውደቅ እና የህዝባችን ጭቆና የሚሳድረውን ህመም ጠንቅቀን እናውቃለን። ደቡብ አፍሪካ እና አልጄሪያ ከፍልስጤም ህዝብ የራስን እድል በራስ የመወሰን ጥያቄ ከጎን እንቆማለን። እስራኤል በጋዛ ህዝብ ላይ የምትፈጽመው አረመኔያዊ ጦርነት መቆም አለበት” ሲሉ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በቅርቡ ለአልጄሪያ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ጠያቄ አቅርበዋል። ራማፎሳ በጋዛ ሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ ሲገልጹ “የሴቶች፣ ህጻናት እና ተዋጊ ያልሆኑ ሰዎች ግድያ፣ በመኖሪያ ቤቶች፣ በትምህርት ቤቶች እና በሆስፒታሎች ላይ የሚደርሰው የቦምብ ድብደባ እና የሰብዓዊ እርዳታ ክልከላው በዓለም ህሊና ላይ ጉድፍ ነው" ብለዋል። "ለዚህ ኢፍትሃዊ ድርጊት ጀርባችንን ልንሰጥ አይገባም። ይህን የዘር ጭፍጨፋ የማስቆም ሃላፊነት አለብን። እስራኤል በጋዛ ህዝብ ላይ ለፈጸመችው ወንጀል ተጠያቂ ልትሆን ይገባል" ብለዋል። ደቡብ አፍሪካ በታህሳስ ወር 2023 በእስራኤል ላይ በዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት ክስ አቅርባለች። ከቱርክ፣ ኒካራጓ፣ ፍልስጤም፣ ስፔን፣ ሜክሲኮ፣ ሊቢያ እና ኮሎምቢያን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት ድጋፍን ያገኘው ይህ ጉዳይ፤ እስራኤልን የ1948ቱን የዘር ማጥፋት ኮንቬንሽን በመጣስ ከሷል። ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ላይ በቅርቡ የእስር ማዘዣ ማውጣቱ የሚታወስ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የእስራኤል ጦር በጋዛ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አውግዘው፤ "አረመኔያዊ ያሉት ጦርነት" እንዲቆም ጠየቁ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የእስራኤል ጦር በጋዛ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አውግዘው፤ "አረመኔያዊ ያሉት ጦርነት" እንዲቆም ጠየቁ
Sputnik አፍሪካ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የእስራኤል ጦር በጋዛ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አውግዘው፤ "አረመኔያዊ ያሉት ጦርነት" እንዲቆም ጠየቁ "እንደ ሀገር የመሬቶቻችን በቅኝ ግዛት ስር መውደቅ እና የህዝባችን ጭቆና የሚሳድረውን ህመም ጠንቅቀን... 09.12.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-12-09T18:08+0300
2024-12-09T18:08+0300
2024-12-09T18:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የእስራኤል ጦር በጋዛ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አውግዘው፤ "አረመኔያዊ ያሉት ጦርነት" እንዲቆም ጠየቁ
18:08 09.12.2024 (የተሻሻለ: 18:44 09.12.2024)
ሰብስክራይብ