የህዳር 30 ረፋድ ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የህዳር 30 ረፋድ ዓበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የእስራኤል ጦር ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ የጎላን ኮረብታን በማለፍ ወደ ሶሪያ ግዛት መግባቱን ሁለት የእስራኤል ባለስልጣናትን ጠቅሶ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። 🟠 ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቮልዲሚር ዘለንስኪ የተኩስ አቁም እና ሰላም እንደሚፈልጉ ተናገሩ። 🟠 የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ-ዮል ካወጁት ጊዘያዊ ወታደራዊ ሕግ ጋር በተያያዘ ከሀገር እንዳይወጡ ሊታገዱ እንደሆነ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። 🟠 የሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት ለቀድሞው የጆርጂያ መከላከያ ሚኒስትር እና ለሚልተን ግሩፕ ኬዘራሽቪሊ መስራች የሚሰራ ዓለም አቀፍ የጥሪ ማዕከላትን በሩሲያ ውስጥ አገኘ። የደህንነት ሃይሎች የሀሰት የጥሪ ማዕከል መረቦቹን የሩሲያ ቢሮ 11 ማናጀሮች እና ሰራተኞች በቁጥጥር ስር አውለዋል። 🟠 የሩሲያ አየር መከላከያዎች በሩሲያ ቤልጎሮድ፣ ሮስቶቭ እና አስትራካን ክልሎች በአንድ ምሽት 13 የዩክሬን ድሮኖችን በማጨናገፍ ማውደማቸውን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0