ባሻር አል-አሳድ እና ቤተሰባቸው ሞስኮ እየደረሱ ነው ሲሉ የክሬምሊን ምንጭ አስታወቁ

ሰብስክራይብ
ባሻር አል-አሳድ እና ቤተሰባቸው ሞስኮ እየደረሱ ነው ሲሉ የክሬምሊን ምንጭ አስታወቁ ሩሲያ በሰብዓዊ ጉዳዮች ምክንያት ጥገኝነት እንደሰጠቻቸው ምንጩ አክሏል። እንደ ምንጩ ገለጻ ሩሲያ ከሶሪያ የትጥቅ ቡድን ተወካዮች ጋር ግንኙነት መስርታለች። የትጥቅ ቡድኑ በበኩሉ በሶሪያ ለሚገኙ የሩሲያ የጦር ሰፈሮች እና የዲፕሎማሲ ተቋማት ደህንነት ዋስትና ሰጥቷል። "ሩሲያ ሁሌም የሶሪያ ቀውስ በፖለቲካዊ መፍትሄ መፈታቱን ትደግፋለች። አቋማችን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጥላ ድርድሮችን በድጋሚ ማስቀጠል ላይ መሰረት ያደረገ ነው" ሲል ምንጩ አመልክቷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0